ኑር-አዳድ ከ1776 እስከ 1760 ዓክልበ. ድረስ (ኡልትራ አጭር) የላርሳ 4ኛ ንጉሥ ነበረ። የሱሙኤል ተከታይ ነበር። የኑር-አዳድ አባት ስም አይታወቅም።

ኑር-አዳድ አዲስ ሥርወ መንገሥት በላርሳ መሠረተ። እንደ ቅድመኞቹ ነገሥታት ሳይሆን ራሱን «አሞራዊ አላለም፣ ስሙም አሞርኛ ሳይሆን አካድኛ ነው። የኑር-አዳድ ማዕረግ አርዕስት ደግሞ እንደ ቅድመኞቹ ነገሥታት «የኡር ንጉሥ» ሳይሆን «የላርሳ ንጉሥና የኡር መጋቢ» ተባለ። ኡር ግን በግዛቱ ውስጥ ቀረች፣ ብዙ የሕንጻ አሠራር በዚያችም ከተማ አስቀጠለ። ኒፑር ወደ ላርሳ ጠላት ወደ ኢሲን ተመለሰ። በአንድ ጽሑፍ ዘንድ «ኑር-አዳድ ከብዙዎች ለንጉሥነቱ ተመረጠ» ይገልጻል።

ለዘመኑ ፲፮ ዓመታት ፲፬ ያህል የዓመት ስሞች ታውቀዋል። ከነርሱም መካከል፦

1776 ዓክልበ. ግ. - «ኑር-አዳድ ንጉሥ የሆነበት ዓመት»
1775 ዓክልበ. ግ. - «ኑር-አዳድ ንጉሥ ከሆነበት ዓመት በኋላ የሆነው ዓመት»
g (ቅድም-ተከተል አይታወቅም) - «ማሽካን-ሻፒር (ከኒፑር ስሜን የነበረ ከተማ) የተያዘበት ዓመት»

የኑር-አዳድ ተከታይ ልጁ ሲን-ኢዲናም ነበረ።

ቀዳሚው
ሱሙኤል
ላርሳ ንጉሥ
1776-1760 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ሲን-ኢዲናም

የውጭ መያያዣ

ለማስተካከል