ተወለደ ብርሃን ገብረ እግዚአብሔር

ተወልደ ብርሃን ገብረ እግዚአብሔር ለማስተካከል

ዶ/ር ተወልደብርሃን ገብረእግዚኣብሔር የእጽዋት ጄኔቲክ ሃብት ለንግድ ሲባል እንዳይለወጥና በተለይ ሰለጠኑ የሚባሉት ኣገሮች የገበሬው ሕብረተሰብ ለዘመናት ጠብቆ ያቆየውን እንዲያከብሩ ተከራክረዋል። ይህ መብት እንዲከበርና የእጽዋትን ጂን እየቀየሩ በፓተንት በመጠበቅ ችግር እንዳይፈጥሩ ኣስተባብረዋል።

ለዶ/ር ተወልደ “ራይት ላይቭሊሁድ አዋርድ” የተባለው ሽልማት በ፲፱፻፺፫ ዓ.ም. ተሰጥቷቸዋል። በእዚህ መስክ ይህ ሽልማት ለዶ/ር መላኩ ወረደ ከመሰጠቱ ሌላ በእንዶድ ምርምር ዶ/ር አክሊሉ ለማ እና ዶ/ር ለገሠ ወልደዮሓንስ ተሸልመዋል። ይህ የዕውቅና ሽልማት የኖቤል ሽልማት በማይሰጥበት መስክ ስለሆነ ኣማራጭ ነው ይባላል።