ዓፄ በካፋ

የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ከ1721 እስከ 1730 ዓ.ም
(ከባካፋ የተዛወረ)

==

ዓፄ በካፋ
በካፋ ለእግዚአብሔር ሲሰግድ የሚያሳይ ስዕል
በካፋ ለእግዚአብሔር ሲሰግድ የሚያሳይ ስዕል
ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ
ግዛት ከ1721- 1730 እ.ኤ.አ.
ተከታይ ዓፄ ዳግማዊ እያሱ
ልጆች ዳግማዊ እያሱ
ሙሉ ስም መሲህ ሰገድ፣ አድባር ሰገድ (የዙፋን ስሞች)
ሥርወ-መንግሥት ሰሎሞን
አባት ቀዳማዊ እያሱ
ሀይማኖት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስትና

==


ዓጼ በካፋ (የዘውድ ስም "መሲህ ሰገድ " ወይም "አድባር ሰገድ") የነገሡት ከእ.ኤ.አ ከግንቦት18፣ 1721 እስከ መስከረም 19፣1730 ነበር። በካፋ የቀዳማዊ እያሱ ልጅ ሲሆን ከሱ ቀድሞ የነገሱት ቀዳማዊ ተክለሃይማኖትሳልሳዊ ዳዊት ወንድም ነበር። ትውልዳቸውም ከ ጎዣም(ጎጃም) ይመዘዛል

አስተዳደጉ

ለማስተካከል

ባካፋ ህጻንነቱን ያሳለፈው ወህኒ አምባ ላይ ነበር። ሆኖም ግን በንጉስ ዮሥጦስ መጨረሻ ዘመን አካባቢ በተነሳ ግርግር ሳቢያ ከወህኒ አምልጦ ከኦሮሞ ቡድኖች ስር ተደበቀ። ሳይቆይም በመማረኩ ለወደፊት እንዳይነገስ አፍንጫው ላይ ጠባሳ ተደረገበት። .[1] ነገር ግን በ1721 ወንድሙ ዳዊት ሳልሳዊ በመርዝ ስለተገደለ ከነበሩት ተወዳዳሪወች እሱ ተመርጦ ነገሠ።

የአገሪቱን ሃይል መዳከም ተከተሎ በመጣ ድንጋጤ ምክንያት በበካፋ ዘመን የነበረችው ኢትዮጵያ በሴራና ተንኮል የተተበተበች እንደንበር ጄምስ ብሩስ ያትታል። ለዚህ ይመስላል ባካፋ "ዝምተኛ፣ ምስጢረኛ፣ ልቡ የማይገኝና በራሱ ባሪያ ወታደሮችና በራሱ ምስል በሰራቸው ሰወች የተከበበ" እንደነበር ሃኪም ይጋቤ መዝግቧል። በንጉሱ ዜና መዋል ላይ የሰፈረው ጽሁፍ የንጉሱን ቆራጥነትና መልካም አስተዳደር ቢያሳይም አላማው ግን የተሰወረ እንደነበር ብሩስ ታዝቧል። [2]

ስርዓተ መንግስቱ

ለማስተካከል

በንጉስ በካፋ ዘመን ብዙ ጦርነት እንዳልነበረና አብዛኛው የንጉሱ ክንድ ያረፈው የተንሰራፋውን የባላባቱን ሃይል ሰብሮ የመካከለኛው መንግስትን ሃይል በማጠናከር እንደነበር ታሪክ አጥኝው ዶናልድ ሌቪን ይናገራል። [3] ታሪክ አጥኝው ፓል ሄንዝ በበኩሉ ለኢትዮጵያ ታሪክ በካፋ ያበርከተው ታላቁ አስተዋጾ ሁለተኛው ሚስቱ ንግስት ምንትዋብ እንደነበረች ይዘግባል።.[4]ጎንደር ከተማን የመጨረሻ ግንቦች ያሰሩት በካፋና ሚስቱ ምንትዋብ ነበሩ።[5]

 
የበካፋ ምግብ አዳራሽ፡ የበካፋ የመጀመሪያው ሚስቱ የተጋበዘችው እዚህ ሲሆን ህንጻውን ያስገነባው እራሱ በካፋ ነው

የመርዝ ሽብርና የበካፋ መጀመሪያ ሚስት

ለማስተካከል

ንጉሱ በካፋ የመጀመሪያ ሚስቱን ካገባ በኋላ የዙፋን ተክሊል ደፋላት። ቀጥሎም ለዚህ ስርዓት ክብር ሲባል በአዳራሽ ውስጥ ግብዣ አድርጎ ሲያበቃ ሚስቲቱ ከቀረበው ምግብ እንደበላች ታመመችና ማታውኑ አረፈች። ከበካፋ በፊት የነበረው ንጉስ በመርዝ ስለሞተና ይቺም ሚስቱ በዚያው እንደሞተች ከፍተኛ ወሬ ስለተናፈሰ ከፍተኛ ሽብር ከተማይቱን አናወጣት።

ከብርሃነ ሞገሴ ጋር እንዴት እንደተገናኙ

ለማስተካከል

በካፋ በህዝብ ዘንድ ክብርን ካስገኘለት ስራው አንዱ ብዙ ጊዜውን በመሰዋትና እራሱን ደብቆ በግዛቱ ሁሉ እየተዘዋወረ ስህተት የተሰራውን ማቃናቱ ነበር። [6] በዚህ ሁኔታ አንድ ቀን ተደብቆ ከጣና ሃይቅ በስተ ምዕራብ ሲጓዝ ቋራ ላይ ታመመና ከአንድ ገበሬ ቤት አረፈ። የዚያ ቤት ባለቤት የብርሃነ ሞገሴ አባት ሲሆኑ እሷም ታማሚውን በካፋ ተንክባክባ ለጤንነት ስላበቃችው ወዲያው አገባት።

ምንትዋብን አገባ

ለማስተካከል

ከላይ እንደተጠቀሰው ከመጀመሪያይቱ ሚስት ሞት በኋላ ከፍተኛ ፍርሃትና ሽብር ይታይ ነበር። ይህ በዚህ እንዳለ ነበር ብርሃነ ሞገሴ ስሟን ቀይራ በንግስና ስሟ ምንትዋብ ተብላ ፋሲል ግምብ የገባችው። በፍርሃትና ጥርጣሬ በተሞላ ከተማ ውስጥ የነበረውን አደገኛ ሴራ ሁሉ ተቋቁማ ነበር ሃይሏን አጠናክራ በኋላም ለከተማይቱ ከፍተኛ አስተዋጾን ያደረገች።

የበካፋ ጥርጣሬ ልክ ማጣት

ለማስተካከል

እየተዘዋወረ መቆጣጠሩ አልበቃው ሲል እ.ኤ.አ 1727 ላይ የህዝቡን ስነ ልቡና ለመፈተን ፈለገ። ለዚህ እንዲረዳው ካሰራው ግምብ ውስጥ በመሸሸግ ለብዙ ቀናት ሳይታይ ጠፋ። በጊዜው የነበሩ መኳንንት በዚ ጉዳይ በመደናገጣቸው ግርግር ተነሳ። ስለዚህም የከተማው ከንቲባ በቤተመንግስቱ ዙሪያ ዘብ አቆመ። ይህ በዚህ እንዳለ ንጉሱ ከተደበቀበት ወጥቶ ወደ ደብረ ብርሃን ስላሴ ቤተክርስቲን ፈረሱን ጋለበ። በሚቀጥለው ቀን ከንቲባው እና ከሱ ጋር አብረውት የሰሩት ሰወች የሞት ፍርድ ተፈረደባቸው። የበካፋን መጥፋት ተከተሎ ከንቲባውና ግብረ አበሮቹ ብቻ ሳይሆኑ የከተማው ህዝቡ ሁሉ በጣም ተደስቶ እንደነበርና በኋላም በህይወት መኖሩን ሲያውቁ በከተማይቱ ሽብር ተነስቶ ብዙው ሕዝብ ከከተያምቱ እንደሸሸ ሃኪም ይጋቤ ይናገራል። ይሁንና ንጉሱ ይቅርታና ምህርተን ስለፈቀደ ሽብሩ በቶሎ ሊያቆም ችሏል። ይህን አስመልክቶ ንጉሱ ሲናገር የጎንደርን ህዝብ እንደሚወድ ግን ህዝቡ በአጸፋው እንደሚጠሉት በምሬት ተናግሯል። .[7]

አዲሱ የታንኳ አይነት

ለማስተካከል

በበካፋ ዜና መዋዕል ላይ እንደተመዘገበ [8] በ1726 ላይ በመጡ ሁለት ግብጻውያን፣ ድሚጥሮስና ጊዮርጊስ፣ የተሰሩ አዲስ አይነት ታንኳወች በጣና ሃይቅ ላይ እየተንሳፈፉ የብዙን ህዝብ ልብ ሰርቀዋል።

በነበረው የሴራና እርስ በርስ ጥርጣሬ ምክንያት በካፋ ዘመን ብዙ ጦርነት አልታየም። ይሁንና በዳሞትበጌምድር እና ላስታ ዘመቻወችን አካሂዷል። የኦሮሞ ቡድኖችንም ሃልይ መግታት ስላልቻለ ምስራቅ ሸዋ በነኝሁ ቡድኖች ቁጥጥር ስር ዋለ፣ ሲዳሞም በዚሁ ከተቀረው ክፍል የተነጠለው በዚህ ጊዜ ነው፣ እንራያ የተባለውም የክርስቲያን አገርም የኦሮሞ ቡድኖች ስለተቆጣጠሩት ከዚህ በኋላ አበቃለት። በዚህ ሁኔታ ሸዋ እራሱን ችሎ በንጉስ አብይ መተዳደር ጀመረ።

ባካፋ የመጨረሻውን የጎንደር ቤተመንግስት አስገንብቶ እ.ኤ.አ. መስከረም 19፣ 1730 ላይ በህመም ምክንያት በሞት አረፈ። የተቀበረውም በደጋ እስጢፋኖስደጋ ደሴትጣና ሃይቅ ነው።

የልጇ ዳግማዊ እያሱ ስልጣን እስኪረጋጋ ድረስ፣ ንግስት ምንትዋብ የባሏን ሞት ለብዙ ጊዜ ደብቃ እንደነበር ታሪክ ይዘግባል።ምክንያቱም ደግሞ ሀገሪቱን የመምራት ፍላጎት ስለነበራት ነው። [9]

 
በንጉሱ የተሰራው የበካፋ ቤተ መንግስት

ማጣቀሻዎች

ለማስተካከል
  1. ^ James Bruce, Travels to Discover the Source of the Nile (1805 edition), vol. 4 pp. 67f
  2. ^ Bruce, Travels to Discover, vol. 4 pp.75f
  3. ^ Donald N. Levine, Wax and Gold: Tradition and Innovation in Ethiopian Culture (Chicago: University Press, 1965), p. 24
  4. ^ Paul B. Henze, Layers of Time, A History of Ethiopia (New York: Palgrave, 2000), p. 104
  5. ^ Levine, Wax and Gold, p.26
  6. ^ Edward Ullendorff, The Ethiopians: An Introduction to Country and People, second edition (London: Oxford Press, 1965), p. 81
  7. ^ Richard K.P. Pankhurst, History of Ethiopian Towns (Wiesbaden: Franz Steiner Verlag, 1982), p. 149.
  8. ^ Translated in part by Richard K.P. Pankhurst in The Ethiopian Royal Chronicles (Addis Ababa: Oxford University Press, 1967).
  9. ^ Hubert Jules Deschamps, (sous la direction). Histoire générale de l'Afrique noire de Madagascar et de ses archipels Tome I : Des origines à 1800. Page 414 P.U.F Paris (1970);