ወህኒ ተራራ በስሜን ጎንደር የሚገኝ ሲሆን በአጼፋሲለደስ ዘመን ለመጀምሪያ ጊዜ ለተገዳዳሪ የነገስታት ወንድ ዘሮች እንደ እስር ቤት አገልግሏል። ይህም እርስ በርስ ጦርነትን ከወደፊቱ ለማስቆም ነበር።

ወህኒ
አምባ ወህኒ (ከሩቁ) በ1851 ዓ.ም.
ወህኒ is located in ኢትዮጵያ
{{{alt}}}
ወህኒ

12°8′ ሰሜን ኬክሮስ እና 37°45′ ምሥራቅ ኬንትሮስ


በቀኝ በኩል፡ አምባ ወህኒ

ፋሲል ልጁ ዳዊት ሲያምጽ ለመጀመሪያ ጊዜ በእስር ወደዚህ ተራራ ልኮታል። የዚህ ስርዓት ምንጭ ቀደምቱ የደብረ ዳሞ እና ግሸን አምባ ዘይቤ ነበር። አጼ ፋሲል ይህን ተራራ ለእስር ቤት ከተጠቀሙበት ጀመሮ እስከ ዘመነ መሳፍንት (በተለይ 1790) ድረስ አምባው በዚህ መልኩ አገልግሏል። በአሁኑ ዘመን የተለያዩ ሰወች ተራራውን ለመውጣት ሞክረው ከአንድ ሰው በስተቀር አልቻሉም ፤ በድሮው ዘመን ግን ቤ/ክርስቲያን እና ቤተ መንግስት በተራራው ላይ ተሰርቶ ነበር። ፍርስራሾቹም አሁን ድረስ በምኩራቡ ይገኛሉ።