ሱሙላኤል
ሱሙላኤል ከ1793 እስከ 1757 ዓክልበ. ድረስ (ኡልትራ አጭር) የባቢሎን ፪ኛ ንጉሥ ነበረ። አባቱን ሱሙ-አቡም ተከተለው።
ለዘመኑ 36 ያህል የዓመት ስሞቹ ታውቀዋል። ከነርሱም መካከል፦
- 1791 ዓክልበ. ግ. - «አሉምቢዩሙ (የካዛሉ ንጉሥ) በመሣርያዎች የተመታበት ዓመት»
- 1781 ዓክልበ. ግ. - «ኪሽ የጠፋበት ዓመት»
- 1776 ዓክልበ. ግ. - «ያህዚሬል ከካዛሉ የተባረረበት ዓመት»
- 1775 ዓክልበ. ግ. - «የኪሽ ግድግዳ የፈረሰበት ዓመት»
- 1774 ዓክልበ. ግ. - «የካዛሉ ግድግዳ የፈረሰበትና ሥራዊቱ በመሣርያዎች የተመታበት ዓመት»
- 1769 ዓክልበ. ግ. - «ያህዚሬል በመሣርያዎች የተመታበት ዓመት»
የሱሙላኤል ተከታይ ልጁ ሳቢዩም ነበረ።
ቀዳሚው ሱሙ-አቡም |
የባቢሎን ንጉሥ 1793-1757 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ ሳቢዩም |