ሰሎሞን ተካልኝ አቋም የለለው ፖለቲከኛ ዘፋኝ ከመሆኑ በፊት ከተዋጣላቸው ኢትዮጵያዊያን ዘፋኞች አንዱ ነበር። ሰሎሞን በተለይ በ70ዎቹ ውስጥ «ወደድ ወደድ» የተባለው ዘፈኑ ነበር ወደ እውቅና ብቅ ያረገው። ሰሎሞን ኢሕአዴጎች ኢትዮጵያን እንደተቆጣጠሩ በስደት ወደ አሜሪካን አገር ሎሳንጀለስ ከተማ ከመጣ በኋላ «ሁሉም ዜሮ ዜሮ» የሚል ዘፈኑን አውጣና ታዋቂነቱን አተረፈ። ከዚያም ጊዜ ጀምሮ ሕይወቱን ከፖለቲካው ዓለም ሙሉ በሙሉ መዝፈቅ ብቻ ሳይሆን ዓላማውንና አቋሙን በመቀያየር በየጊዜው ዲያስፖራውን ግራ ሲያጋባ ኖሮአል። በራሱ ላይ ና በእጁ የባንዲራ መሓረብ በማሰር በየአደባባዩ ከመታየቱም ሌላ በየራዲድዮ ጣቢያዎችና በየፓልቶክ ሩም ውስጥ ጸረ ኢሕአዴግ አስተያየቶች እየሰጠ ከዘፋኝነት ወደ ሙሉ ጊዜ ፖለቲከኛነት በይፋ ተሸጋገረ። በዚህም ሳያበቃ በ2007 እ.ኤ.አ. ወደ አሥመራ በመጓዝ ከአቶ እሳያስ አፈወርቂ ጋር በመገናኘት እንዴት ወያኔ መወገድ እንዳለበት ተመካከረ። ከአቶ ኢሳያስና ከካቢኔ አባሎቻቸው ጋር አብረዋቸው የማስተዋሻ ፎቶም ተነሳ። በ3 ተከታታይ ልዩ ፕሮግራም በኤርትራ ቲቪ የአማርኛ ቋንቋ ሥርጭት አቶ መለስን እንዲሁም ወያኔን ሲዘልፍና ሚስጢር ብሎ ያለውን ሁሉ ተናገረ። አሬንጓዴ ነብራማ ወታደራዊ ዩኒፎርም ለብሶና ቀይ መለዮ አርጎ «የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር» ነን ከሚሉ ከብዙ መቶ ወጣቶች ጋር በዕንባ ስሜታዊ የሃገር ፍቅር ዘፈኖች ሲያዜም አመሸ። በፍጹም አልርሳችሁም እያለ ሁሉንም ሲያቅፍና አይዞአችሁ ሲል በቪዲዮ ማስታወሻ መቀዳቱ በዩ ቱብ ተመዝግቦ ይገኛል።

በ2008 ድንገት ሰሎሞን ተካልኝ ብድግ ብሎ ጓዙን ጠቅልሎ ወደ አገር ቤት ገባ። በጊዜው ብዙዎቹን አስደነገጠ። ይሁን እንጂ ሰሎሞን ተካልኝ የተማመነውን ተማምኖ ኖሮአልና ከወያኔ ጋር ቅድመ ስምምነት አርጎ ኖሮ ገና አዲስ አበባ ኤርፖርት እንደደረሰ የመንግሥት ጋዜጠኞች መቅረጸ ድምጻቸውን ይዘው ጠበቁት። ገና እንደደረሰም መሬቱን ዝግ ብሎ ሳመ፡ ቀና ብሎ እጆቹን ወደ ላይ ዘረጋና ለዚያ ያበቃውን አምላኩን አመሰገነ። ከእንባው ጋር እየታገለም ውጭ አገር ባሳለፉት ዘመናት ሁሉ ስለ ኢሕአዴግ የተሳሳተ ግንዛቤ እንደነበረው ለመናገር አንድ ሰዓት ከ20 ደቂቃ ጊዜም አልፈጀበትም። ገና ቀና ብሎ በአቅራቢያው ያሉትንም ሰዎች በደንብ ሳይለይ የአገሪቱንም ዕድገት ማሞጋገስና ዲያስፖራውንም ለመወረፍ አፍታ አልፈጀበትም።

ሰሎምን ተካልኝ እነኛ በንባ ሲቃ እየታጠበ ቃል የገባላቸውን የአሥመራ አርበኞች ወጣቶች ጉዳይ ረስቶ ዘንድሮ በተደረገው ምርጫ ኢሕአዴግ እንዲያሸንፍ የቅስቀሳ ዘፈን አውጥቶ አቶ መለስ ዜናዊን በማወደስ እንዲህ ሲል አቀነቀነ። << ይቅጥል ይቀጥል ሊቁ ሰው .... ይቀጥል ከፊት ሆኖ ይምራን ይቀጥል እኛ እንከተልው ከድል ጋር ጉዞ አልጠገብንምና አሁንም ይቀጥል ....... በብልህ አመራሩ በዓለም ተወድሶአል ..... ትናንት ብቻ አይደለም ዛሬም የመረጣል >>

ሙሉ ዘፈኑን ለማየት የሚቀጥለውን ሊንክ ይጫኑ http://www.youtube.com/watch?v=js-VtDkMAvA

በመጨረሻም ይህች ግጥም ከዩ ቱብ ተወሰዳለችና መታሰቢያነቷ ለአቶ ሰሎሞን ተካልኝ ትሁን። http://www.youtube.com/watch?v=l79VeFNpXK0