ሰልና ሜሪ ጎመዝ (ተወለደች ሀምሌ ፲፬፣ ፲፱፻፹፬) አሜሪካዊት ዘፋኝተዋናይት ናት። ሰልና፣ የትወና ህይወቷ ገና በልጅነቷ ሲጀምር ተሳትፋ ባርኒ ኤንድ ፍረንድስተለቭዥን ተከታታይ ላይ (፲፱፻፺፬-፲፱፻፺፮) እና በዛው የእድሜ ክልል ውስጥ አለክስ ሩሶ የተባለ ገጸ ባህሪን በድዝኒ ቻነል የተለቭዥን ተከታታይ ውዘርድ ኦቭ ዌቭርሊ ፕሌስ (፲፱፻፺፱-፳፻፬) ላይ ተጫውታ ወደ ዝናው መጣች እንደ ተዋናይት፤ እንደ አቀንቃኝት ከፖፕ ሮክ ቡድኗ ሰልና ጎመዝ & ዘ ሲንጋ እውቅና ብታገኝም የአሁን እሷነቷ በይበልጥ መገንባት የጀመረው በግል ባደረገችው ጉዞ ነው የመጀመሪያ አልበሟ እስታርዝ ዳንስ በ፳፻፭ ተለቀቀ የመጀመሪያ ምርጥ አስር ሙዚቃዋን የያዘው።

ሰሊና ጎመዝ

እስከ ፳፻፱ ድረስ ሰልና ሽጣለች ከ፯ ሚልየን በላይ አልበሞች እና ከ፳፪ ሚልየን በላይ ነጠላዎች በአለምአቀፍ ይህ መረጃ ቢልቦርድን መሰረት አድርጎ። የተለያዩ ሽልማቶችን ስትወስድ ቢልቦርድ ሰይሟት ነበር "የአመቱ እንስት" በ፳፻፱። ማህበራዊ ድረገጾች ላይ አያሌ ክተላዎች ሲኖሯት በአንድ ወቅት ይበልጡን ተከታዮች በማፍራት ቀዳሚ ነበረች እንደ ግለሰብ፣ እንስትግራም ላይ። የሰልና ሌሎች የስራ ሙከራዎች ይካተታሉ፦ የመቀባቢያ፣ የአልባሳት፣ የሽቶ፣ እና የእጅ ቦርሳ ስራ ሙከራዎች። ሰልና ከብዙ ረጂ ተቋማትጋ አብራ የሰራች ሲሆን አገልግላለችም እንደ የዩንሰፍ አምባሳደር ከእድሜዋ ፲፯ ጀምሮ።


የቀድሞ ህይወት ለማስተካከል

ሰልና ተወለደች በ፲፱፻፹፬ ከአባቷ ርካርዶ ጆውል ጎመዝ እና ከመድረክ ተዋናይት እናቷ አማንዳ ዶውን ኮርንት። ስሟ የተሰየመው ከቲዠኖ አቀንቃኝቷ ሰልና ኩወንታኒላ በኋላ ነው። አባቷ የሜክሲኮ ዘር ሲኖረው እናቷ ደግሞ የተወሰነ የጣልያን። የህስፓንክ ማንነቷን አስመልክቶ ሰልና ብላለች እንደሆነች "የኩራት የሶስተኛ ትውልድ አሜሪካዊ፡ሜክሲኮአዊ" ፡ "ቤተሰቦቼ የኩንሲንረስ አከባበር አላቸው ፡ ወደ ኮምንየን ቤተ ክርስትያን እንሄዳለን፣ ካቶልክ የሆነ ምንም ነገር እናደርጋለን፣ ግን ባህላዊ ነገሮች ብዙም የሉንም መናፈሻ ሄዶ ባርብኪው ከማድረግ ውጪ እሁድ እሁድ ከቤተ ክርስትያን መልስ"። ሰልና የአባቷ ሀገር ቋንቋ የሜክሲኮ እስፓንሽን አቀላጥፋ መናገር ትችል ነበር እስከ እድሜ ሰባት ፡ በአምስት አመቷ ከእናቷጋ ብቻ ለመቅረት ሁኔታው አስገድዷት ነበር፦ የወላጆቿ መፋታት ፡ ሰልና ሁለት ታናናሽ ግማሽ እህቶች አሏት—አባትና እናቷ በፈጠረቱ ሌሎች የየብቻ ትዳሮች። ሰልና ተወለደች እናቷ የ፲፮ አመት ልጅ ሳለች ፡ ቤተሰቡ ገንዘብ ነክ ጉዳዮች ላይ ችግር ነበረበት በሰልና የልጅነት እድሜዎች ውስጥ ፡ ሰልና አንስታለች የአንድ ዶላር ሩብ መፈለግ እደነበረባቸው ለመኪና በንዚን ለማግኘት ብቻ ፡ "ፈርቼ ነበር ቤተሰቦቼ አንድ አልነበሩም፣ መቼም ብርሀን አይቼ አላውቅም ነበር በሸለቆው ጫፍ እናቴ ጠንክራ በምትሰራበት ለኔ የተሻለ ህይወት ለማቅረብ ፡ ምን ልሆን እንደምችል ሰግቼ ነበር እዛ (ቴክሳስ) ምቆይ የነበረ ቢሆን"። "እናቴ ጠንካ ነበረች በዙሪያዬ፣ እኔን በአስራ ስድስት አመቷ መውለዷ ትልቅ ሀላፊነት ነው፤ ሁሉን [ትታለች] ለኔ ብላ ሶስት መተዳደሪያ ስራዎችን ይዛለች፣ ደግፊኛለች፣ ህይወቷን መስዋዕት አድርጋልኛለች"። ሰልና በልጅነቷ ከአያቶቿ ጋ ቅርብ ግንኙነት የነበራት ሲሆን አሳልፋለች የተለያዩ የህዝብ በአላትን ከነሱጋ ከፍ ባለችበት ጊዜ ፤ ወላጆቿ ማስተማርን ሲጨርሱ ብዙ አነሱ አያቶቿ ነበር የሚንከባከቧት። ብላለች፦ "አሳድገውኛል" እስካገኘች ድረስ የስኬት ጅማሮን በትእይንት ፕሮግራሞች።

የስራ ታሪክ ለማስተካከል

ከትወና ሙያዋጋ እነዚ ፊልሞች (ተከታታዮች) ላይ ሰርታለች፦ አናዘር ስንደረላ እስቶሪ (፳፻)፣ ፕርንሰስ ፕሮተክሽን ፕሮግራም (፳፻፩)፣ ውዘረድ ኦቭ ዌቨርሊ ፕሌስ ፡ ዘ ሙቪ (፳፻፩)፣ ርሞና ኤንድ ቢዙስ (፳፻፪)፣ ሞንቴ ካርሎ (፳፻፫)፣ እስፕሪንግ ብሬከርስ (፳፻፬)፣ ጌት እዌይ (፳፻፭)፣ ዘ ፋንድመንተልስ ኦቭ ኬሪይንግ (፳፻፰)፣ ዘ ደድ ዶንት ዳይ (፳፻፲፩)፣ ኧ ሬይኒ ዴይ ኢን ንው ዮርክ (፳፻፲፩)፣ ኦንሊ መርደርዝ እን ዘ ቢውልዲንግ (፳፻፲፬-ሚቀጥል)፣ እና ሆተል ትራንስልቨንያ (፳፻፬-የቀጠለ)። በአስተዳዳሪነት አግዛለች የነት ፍለክስ ተከታታዮችን፦ 13 ሪዝንስ ዋይ (፳፻፱-፳፻፲፪) እና ልቪንግ አንዶክመንትድ (፳፻፲፩) በአጋዥ፡ኩባንያዋ ስር።

ለቃለች ፫ አልበሞች ከቡድኗ ሰልና ጎመዝ & ዘ ሲንጋ እና ሶስቱም አስር ውስጥ ገብተዋል ከቢልቦርድ ተመስክረዋልም የወርቅ በዘ ርኮርዲንግ ኢንደስትሪ አሶስዬሽን ኦቭ አሜሪካ፦ ኪስ & ተል (፳፻፩)፣ ኧ ይር ውዝአውት ሬይን (፳፻፪) እና ወን ዘ ሰን ጎዝ ዳውን (፳፻፫)። የግል ሶስት አልበሞቿ፦ እስታርዝ ዳንስ (፳፻፬)፣ ርቫይቨል (፳፻፯) እና ሬር (፳፻፲፪) ሁሉም አንደኝነት ላይ የተቀመጡ። አስር ውስጥ የገቡላት ዘፈኖቿ፦ "ከም & ጌት እት"፣ "ዘ ሀርት ወንትስ ዋት እት ወንትስ"፣ "ጉድ ፎር ዩ"፣ "ሴም ኦልድ ሎቭ"፣ "ሀንድስ ቱ ማይሰልፍ"፣ "እት ኤንት ሚ"፣ እና የመጀመሪያ ቁጥር አንድ ዘፈኗ "ሉዝ ይው ቱ ሎቭ ሚ"።

የሙዚቃ አይነት ለማስተካከል

ሰልና የምትገለጸው እንደ ፖፕ አርቲስት ሲሆን ስራዎቿ ይከፋፈላሉ በአይነተ ሙዚቃዎች፦ ዳንስ፡ፖፕ እና ኢዲኤም፤ ሌሎች የሙዚቃ አይነቶችን መሞከሯ እንዳለ ሆኖ ፡ የመጀመሪያ አልበሟ ከቡድኗ ዘ ሲንጋ የለቀቀችው የኧለክትሮንክ ሮክ እና የፖፕ ሮክ ተጽእኖች ሲኖርበት አከታትላ ከዚ ቡድኗጋ የለቀቀቻቸው ዘፈኖች የዳንስ፡ፖፕ ድምጸ ምርጫ አለባቸው ፡ "ኧ ይር ዊዝአውት ሬይን" አልበም ታውቋል በስንት፡ፖፕ ባህሪያቶቹ፣ "ወን ዘ ሰን ጎዝ ዳውን" አልበም ደግሞ በይበልጥ ኧለክትሮፖፕ እና ድስኮፖፕ ዘውጎችን አካቷል። የግል የመጀመሪያ አልበሟ "እስታር ዳንስ" እጅጉን የኢዲኤም፡ፖፕ ተጽዕኖ የነበረበት ሲሆን የኧለክትሮንክ፣ ድስኮ፣ ተክኖ፣ እና የዳንስሆል ሙዚቃዊ ባህሪያቶች ነበሩበት። ዘፈኖቿ፦ "ዘ ሀርት ወንትስ ዋት እት ወንትስ" እና "ጉድ ፎር ዩ" በይበልጥ ጎልማ ፖፕን ነው ያስተዋወቁት በየክፍላቸው።

ተጽእኖ ለማስተካከል

ሰልና፣ ቀደም ባሉ ጊዜያት ብሩኖ ማርስን እንደ ተፅኖዋ ገልፃው ነበር፦ "የሙዚቃ አይነቱ በአጠቃላይ [ሁኔታው]፣ [በሙዚቃ] የሚቀርብበት መንገድ፣ እራሱን የሚይዝበት መንገድ" ብላለች። ክርስቲና አግወሌራብርትኒ እስፒርስቢዮንሴሪሀናቴይለር እስዊፍትንም እንደ ተፀዕኖ ጠቅሳቸዋለች እነማ "እስታር ዳንስ" እና "ርቫይቨል" አልበሞቿ ላይ ተፅዕኖ ያሳደሩ የፖፕ ንጉሱ ማይክል ጃክሰን እህት ጃነት ጃክስን ተካታበት።