ራዲዮ
ራዲዮ ራዲዮ ሞገዶችን በመከርከም መልዕክት ከቦታ ቦታ የሚተላለፍበት ቴክኖሎጂ ነው። [1] ራዲዮ ሞገድ የብርሃን አይነት ሞገድ ሲሆን ልዩነቱ የራዲዩ ሞገድ የብርሃንን ያኽል አይርገበገብም። የራዲዮ ሞገድ በአየርም ሆነ በወና ውስጥ የሚጓዘው የኤሌክትሪክ መስኩን በማርገብገብና ሞገድ በመፍጠር ነው። ይህን ሞገድ ባህርዩን በዘዴ በመቀየር (በመከርከም) መልዕክት እንዲያዝል ተደርጎ ይላካል። ለምሳሌ የራዲዮ ሞገዱን ቁመት በአንድ ድምፅ ሞገድ ትክክል ተከርክሞ ሲጫን ኤ.ኤም ራዲዮ ይፈጠራል። በራዲዮ ሞገዱ ድግግሞሽ ላይ ሲጫን ደግሞኤፍ.ኤም ራዲዮ ይሆናል። በሞገዱ ቅድመት ላይ ሊጫን ይችላል፣ ሆኖም ይሄ ብዙ ጊዜ የተለመደ አይደለም። በድምፅ ሞገድ ትክክል የተከረከመው የራዲዮ ሞገድ ኤሌክትሪክ አስተላላፊ ቁስ ሲያጋጥመው በቁሱ ውስጥ ተለዋዋጭ የኤሌክትሪክ ጅረት ይፈጥራል። ይህን ተለዋዋጭ ጅረት የሚተረጉሙ መሳሪያወች የተጫነውን ድምፅ ከራዲዩ ሞገዱ አውርደው ወደ ስፒከሩ በመላክ የራዲዮ ዝግጅት እንዲደመጥ ይሆናል። ከድምፅ በተጨማሪ የምስል መልዕክትም ሊላክ ይችላል፣ በዚህ ወቅት የቴሌቪዥን ዝግጅት እንዲታይ ይሆናል።
ታሪክ
ለማስተካከልየራዲዮ ቴክኖሎጂ ብዙ ተማሪወችንና ብዙ ጊዜ የወሰደ ጥረት ነው እንጂ ያንድ ሰው ድንገተኛ ፈጠራ አይደለም። ሆኖም አንድ አንድ ተማሪወች ከሌሎች በተለየ መልኩ ጉልህ አስተዋጾ ስላደረጉ በታሪክ ተጠቃሽ ናቸው፣ ከነዚህ ውስጥ ቶማስ ኤድሰን፣ ኒኮላ ቴስላ እና ጉልየልሞ ማርኮኒ ዋናዎቹ ናቸው። በ1885 ዓ.ም. ኒኮላ ቴስላ እንዴት መልዕክትን ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ያለ ሽቦ ማስተላለፍ እንዲቻል አሳየ [2]። ከዚያ በኋላ ተመራማሪወች፣ አንዱ ያንዱን ስራ በማሻሻል በ1887 ዓ.ም. ማርኮኒ ያለ ሽቦ መልዕክትን ከአንድ ቦታ ወደሌላ ሩቅ ቦታ የሚያስተላልፍ ስርዓት በተጨባጭ በመገንባት (2.4 ኪሎ ሜትር) በሚቀጥለው አመት ደግሞ ከእንግሊዝ አገር ለራዲዮ ፈጠራ ፓተንት በማግኘት አሁን ድረስ ስሙ ተጠቃሽ ነው። በ1889 ማርኮኒ የመጀመሪያውን የራዲዮ ማሰራጫ በአይል ኦፍ ራይት፣ እንግሊዝ በመክፈት እንዲሁም የራዲዮን ማምረቻ ፋብሪካ በማቋቋም ስሙ ከራዲዮ ፈጠራ ጋር እንዲቆራኝ ሆነ።
- ደግሞ ይዩ
- የራዲዮ ቴክኖሎጂዎች
- ኅልዮት
ማጣቀሻ
ለማስተካከል- ^ Dictionary of Electronics By Rudolf F. Graf (1974). Page 467.
- ^ IEEEVM: Nikola Tesla