ክሪስታል ራዲዮ የሚሰኘው ከሁሉ በላይ በጣም ቀላል ራዲዮ ተቀባይ ሲሆን፣ በድሮው የራድዮ ዘመን ታዋቂነት ያገኘ ነበር። ክሪስታል ራዲዮ ባትሪም ሆነ ሌላ የኤሌክትሪክ ኃይል አይፈልግም። ይልቁኑ ከሚተላለፍ የራዲዮ ሞገድ አቅም በመውሰድ በራሱ ይሰራል። ለዚህ ተግባር ሲባል ክሪስታል ራዲዮ ረጅም የሽቦ አንቴና ይፈልጋል። ክሪስታል መባሉ ድሮ ይሰራበት ከነበርው ወሳኝ ክሪስታል ጋሌና የተባለ ክፍል የመጣ ስም ነው። በአሁኑ ዘመን ይህ ክፍል በዳዮድ ተተክቷል። ክሪስታል ራዲዮ በጣም ቀላል ከመሆኑ የተነሳ ማንም ሰው ሊሰራው ይችላል። የሚያስፈልጉትም እቃወች አንቴና ሽቦ (ረጅም መሆነ አለበት)፣ ጣቢያ መቀየሪያ ጥቅል ሽቦ (መዳብ) ፣ ክሪስታል ጠቋሚ ወይንም ዳዮድ እና የጆሮ ስልክ (ማለቱ ማናቸውም በጆሮ ላይ ተደርጎ ሙዚቃ ለመስማት የሚያገለግል ኢር ፎን) ናቸው። በርግጥ የክሪስታል ራዲዮ የተወሰነ ጣቢያወችና በዚያው ልክ ድምፁም ከፍተኛ ስላልሆነ ኢር ፎን መጠቀም ግድ ይላል።

ሌላ አይነት የክሪስታል ራዲዮ ዲዛይን። የኢርፎን አቀማመጡን በግልጽ በሚያሳይ መልኩ
1- ጥቅልል ሽቦ -- የመዳብ -- ቢያንስ ቢያንስ 120 ጊዜ የተጠቀለለ -- እርስ በርሱ የማይነካካ (ኢንሱሌትድ)
2- የጥቅልል ሽቦውን አስተላላፊ ክፍል መጠን መምረጫ እጀታ። ኤሌክትሪክ አስተላላፊ መሆን አበት -- ጣቢያ መቀየሪያ
3- ወደ መሬት የሚቀበር ሽቦ የሚያያዝበት። ቀዝቃዛ ውሃ ተሸካሚ የቧምቧ ውሃ ቱቦ ጋር ማያያዝ ነገሩን ያቃልላል።
5- ከአንቴና ገመድ ጋር የሚያያዝ። እስከ 20ሜትር ገመድ ያስፈልጋል፣ የጠራ ሲግናል ለማግኘት። በአካባቢ ያለን እንደ አሸንዳ ወይም ሌላ አይነት ብረትን በሽቦ በማገናኘት የሽቦውን መጠን ማሳነስ ይቻላል።
6- ከ4 እስከ 1000 ፒኮ ፋራድ ካፓሲተር (ይህ ከአረጀ ራዲዮ ወይንም ቴሌቪዥን ወይንም ማንኛውም አይነት ኤሌክትሮኒክስ ውስጥ ሊገኝ ይችላል)።
7- ዳዮድ፣ ከአረጀ ራዲዮ ወይም ሌላ ኤሌክትሮኒክስ ማግኘት ይቻላል። ካልተቻለ ከጎን 7a እንደሚታይ በቤሳመርፌ ቁልፍ መተካት ይቻላል። በመርፌ ቁልፉ ቦታ የእርሳስ ውጡን መጠቀም ይቻላል።
8- ሬዚስተር
9- የጆሮ ስልክ ወይም ኤር ፎን እዚህ ላይ ሊገጠም ይገባል። ማንኛውም ሲዲ ማጫወቻ ላይ የሚገጠም የጆሮ ስልክ ሊሰራ ይቻላል።

አሰራርና አጠቃቀም

ለማስተካከል

ቀላል የአሰራር ዘዴ

ለማስተካከል
 
ይህ እሚታየው ምስል ለተወሰኑ የአጭር ሞገድ ራዲዮ ጣቢያወች የሚሰራ ነው።

ይህ የሚታየው የክሪስታል ራዲዮ የሽቦ ዑደት፣ ቀላል ልዲዛይን ሲያሳይ ነገር ግን የሚያቀበለው ጣቢያ ከአጭር ሞገዶች በላይ መሻገር አይችልም። ከምስሉ እንደምንረዳ ጣቢያ መቀየሪያው ከትይዩእና ተያያዥ አንድ ወጥ ጥቅልል ሽቦወችና ከተለዋዋጭ ካፓሲተር የተሰራ ነው። አንቴናውና መሬቱ በትዩዩ መንገድ የተገናኙ ናቸው። ክሪስታል ራዲዮኖች አንቴናቸው ቢያንስ ቢያንስ 20 m (ሜትር) ርዝመትና 6 m ከፍታ ሊኖረው ያስፈልጋል። ይህ ጉዳይ በሚፈጥረው የካፓሲተር ውጤት ከተወሰኑ ራዲዮ ጣቢያወች በላይና በታች ለመቀበል አዳጋች እንዲሆን ያደርጋል። ሆኖም ግን ከካፓሲተሩ ይልቅ የሽቦ ጥቅልሉን ተለዋዋጭ በማድረግ ብዙ የራዲዮ ጣቢያወችን መቀብል ይቻላል።

የበለጠ ለማንበብ

ለማስተካከል

አጠቃላይ መረጃ

ለማስተካከል

ተጨማሪ ንባብ

ለማስተካከል