ጉግሣ
ራስ ጉግሣ በኢትዮጵያ ዘመነ መሳፍንት ከ1792 እስከ 1817 ዓም ድረስ የበጌምድር ራስ፣ የየጁ ስርወ መንግስት እንደራሴ ነበሩ። የመርሶ ባሬንቶ እና የራስ ዓሊጋዝ እኅት የከፈይ ልጅ ነበሩ።
በእንግላንድ ተጓዥ ናታንየል ፒርስ ጽሑፍ መሠረት፣ ወልደ ሚካኤል የሚል የክርስትና ስም ተቀበሉ።[1] ዘመናቸው የሥርወ መንግሥቱ ጫፍ ተብሏል።[2]
ከሴት ልጆቻቸው አንዲቱ ለደጃዝማች መሩ ዘደምቢያ፣ ሌላይቱም ሂሩት ለደጃዝማች ኃይለ ማርያም ተጋባች።[3]
ዜና መዋዕሎች እንደሚሉ፣ ጉግሣ የበጌምድር ራስ በሆኑ ጊዜ ዋና ከተማቸውን በተራሮች ከጎንደር 60 ኪሎሜትር ወደ ደቡብ ምሥራቅ ሌቦ በተባለ ሥፍራ አደረጉት።[4] ጉግሣ እንደራሴ እየሆኑ፣ ከበጌምድር መኳንንት መሬትን ያዙባቸው፣ ንጉሠ ነገሥቱም በስም ብቻ ቀሩ። በ1792 ዓም የመሬት ይዞታ ከጉልት ወደ መንግሥት ንብረት እንዲቀየር በንጉሥ ስም ዐወጁ። በመጀመርያው፣ ገበሬዎቹ ከጉልተኞቹ ነጻ ስለ ወጡ ደስ አሉ። ሆኖም ከዚያ ራስ ጉግሣ የታላላቆቹን ቤተሠቦች መሬት በየዓመቱ በየሰበቡ እየያዙባቸው ስለ ሆነ፣ ገበሬዎቹ የሚጠብቁዋቸውን የሚከራክሩላቸውንም አጡ። አቶ ሪቻርድ ፓንክኸርስት እንደ ጻፉ፣ «ይህም እየሆነ፣ መሬታቸው የጠፋባቸው መኳንንቱ ሁሉ ያህል ቅጥረኛ ወታደሮች ሆኑ። አንዳንዴ ሙሉ መንደሮች አገራቸውን ትተው ወደ ጎረቤት አገር ይፈልሱ ነበር፤ መኳንንቱ እንዲህ ነጣቂዎች ሆኑና። ከገበሬዎቹም ወገን ብዙዎች ወደ ጭፍሮች ገቡ፤ የሥራዊት ኑሮ ከእርሻ አገልግሎት መረጡና።»[5]
በ1795 ዓም ራስ ጉግሣ በኢኦተቤ ውስጥ በታየው ትምሕርታዊ ክርክር ውስጥ ገቡ። የእጨጌ ወልደ ዮና ወገን ደግፈው የተቀራኒ «ቅባት» ወገን ከበጌምድር ለቅቆ እንዲወጣ አደረጉ። በዚያንም ወቅት ያህል አቡና ፫ኛው ዮሳብ ሲያርፉ ቤተ ክርስቲያኑ እየደከመች ራስ ጉግሣ በመስከረም 1 1796 ዓም የቤተ ክርስቲያኑን ቦታዎች ዘረፉ።[6]
ዋቢ ምንጮች
ለማስተካከል- ^ Pearce, The Life and Adventures of Nathaniel Pearce, edited by J.J. Halls (London, 1831), vol. 1 p. 70
- ^ Bahru Zewde, A History of Modern Ethiopia, 1855-1994, second edition (Oxford: James Currey, 2001), p. 12; Henze, Layers of Time (New York: Palgrave, 2000), p. 122.
- ^ Mordechai Abir, Ethiopia: The Era of the Princes; The Challenge of Islam and the Re-unification of the Christian Empire (1769-1855) (London: Longmans, 1968), p. 32.
- ^ Richard P.K. Pankhurst, "The History of Däbrä Tabor (Ethiopia)", Bulletin of the School of Oriental and African Studies, 40, (1977), p. 235
- ^ Richard Pankhurst, Economic History of Ethiopia, 1800-1935 (Addis Ababa: Haile Selassie I University Press, 1968), pp. 137ff.
- ^ Donald Crummey, Priests and Politicians, 1972 (Hollywood: Tsehai, 2007), p. 25; the date is from H. Weld Blundell, The Royal chronicle of Abyssinia, 1769-1840 (Cambridge: University Press, 1922), p. 474
ቀዳሚው ዓሊጋዝ |
የጁ ስርወ መንግስት | ተከታይ ይማም |