ሞዴትግዕዝ ቀለም ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኮምፕዩተር የገባበት ቃላት ማተሚያ ነው። ስሙን ያገኘው ሞደርን ኢትዮጵያ (Modern Ethiopia) የሚሉትን ቃላት ወደ ሞዴት (ModEth) በማሳጠር ነው። በእጅ ጽሑፍና ማተሚያ ቤቶች ብቻ ይታተም የነበረው የግዕዝ ፊደል በማይክሮሶፍት ዲስክ ኦፐሬቲንግ ሥርዓት ለገበያ ዩናይትድ እስቴትስ ውስጥ ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ በኣደረጉት በዶ/ር ኣበራ ሞላ በ፲፱፻፹ ዓ.ም. ቀረበ። ይህ የኢትዮጵያ ኮምፕዩተሮችና ሶፍትዌር ኩባንያ ፕሮግራም ከዓማርኛው ቀለሞች ሌላ የትግርኛትግረኦሮሚፋጉራግኛና የኣገው/ቢለን ቀለሞች ትንሽ ቆይቶ ትሩታይፕ ሆነው ተጨመሩ። ብዛቱ ወደ 480 የነበረው ኣንድ የግዕዝ ቀለም ስምንት የእንግሊዝኛ ፎንቶች ላይ ተበትኖ ከኣንድ የእንግሊዝኛ ፊደል ጋር ነበር የቀረበው። ሆህያቱ የተከተቡት የፈንክሽን መርገጫዎችና እያንዳንዱን የመርገጫ ቁልፎች በማጣመር በሁለት መርገጫዎች ነበር። ሁለት የፊደል ገበታዎችና የፊደል መለጠፊያዎች ነበሩት።

ሞዴት የግዕዝና እንግሊዝኛ ቃላት ማቀነባበሪያና ማተሚያ ነበር። የኢትዮጵያ ኮምፕዩተሮችና ሶፍትዌር ለኣዲስ ኣበባ ዩኒቨርሲቲ በ፲፱፻፹፭ ዓ.ም. ሞዴትን በነፃ ኣበርክቶ ነበር።

የሞዴት መሻሻል በ፲፱፻፹፮ ዓ.ም. ተቋርጦ ማይክሮሶፍት 3.1 ተወዳጅነት እንዳገኘ በኢትዮወርድ ተተካ።

የሞዴት ፊደል ፲፱፻፹፫ ዓ.ም. Ethiopian Review, 1991

የውጭ መያያዣዎች ለማስተካከል