ሞሪሸስሕንድ ውቅያኖስ ውስጥ በማዳጋስካር አጠገብ የተገኘው ደሴት አገር ነው። ከ፩ ሚሊዮን ኗሪዎች በላይ አሉበት። በ1960 ዓም ነፃነት ከዩናይትድ ኪንግደም አገኘ።

የሞሪሸሰ ሪፐብሊከ

የሞሪሸሰ ሰንደቅ ዓላማ የሞሪሸሰ አርማ
ሰንደቅ ዓላማ አርማ
የሞሪሸሰመገኛ
የሞሪሸሰመገኛ
ዋና ከተማ ፖርት ሉዊስ
ብሔራዊ ቋንቋዎች እንግሊዘኛ (ይፋዊ) ፥ ፈረንሣይኛ
መንግሥት
ፕሬዚዳንት
ጠቅላይ ሚኒስትር
 
አሜናህ ጉሪብ
ፕራቪንድ ጀግናውጥ
የመሬት ስፋት
አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.)
 
2,040 (179ኛ)
ገንዘብ የሞሪሸሰ ሩፒ
ሰዓት ክልል UTC +4
የስልክ መግቢያ +230

እስከ 1673 ዓም ድረስ ሕልውና የነበረው የታላቅ ወፍ ዝርያ ዶዶ በሞሪሸስ ብቻ ይገኝ ነበር፤ በዚያውም ወቅት መጨረሻው የዶዶ ወፍ አለቀ። የሰው ልጆች ግን እስከ 1500 ዓም ያህል ድረስ አልኖሩበትም። ከዚያ የኔዘርላንድና የፈረንሳይ ሰዎች ይሠፈሩበት ነበር።

ሸንኮራ ኣገዳ የሞሪሸስ ዋነኛ ምርት ነው፤ ከዚህም አረቄ ይሠራል። ኗሪዎቹ አሁን በብዛት ከሕንድ ስለ ሆኑ፣ ከግማሽ በላይ የሂንዱ ሃይማኖት ተከታዮች ናቸው። የተወደዱት እስፖርቶች እግር ኳስራግቢ ናቸው።