ሜድትራኒያን ባሕር
ባህር
(ከሜዲቴራኒያን የተዛወረ)
ሜድትራኒያን ባሕር አብዛኛው ክፍሉ በአፍሪካ ፣ አውሮፓ እና እስያ የተከበበ ባሕር ነው። 2.5 ሚሊዮን ካሬ ኪ.ሜ. ይሸፍናል።
![](http://upload.wikimedia.org/wikipedia/commons/thumb/2/2c/Mediterranean_Relief.jpg/320px-Mediterranean_Relief.jpg)
«ሜድትራኒያን» የሚለው ስም ከሮማይስጥ ሲሆን ትርጉሙ «ከአህጉሮች መካከል» ነው። በግዕዝ ደግሞ ስሙ «ባሕር ዐቢይ» (ታላቁ ባሕር) ይባላል።
የሚያካልሉ ሀገሮች
ለማስተካከል- አውሮፓ ፦ ስፔን ፣ ፈረንሳይ ፣ ሞናኮ ፣ ጣልያን ፣ ማልታ ፣ ስሎቬንያ ፣ ክሮሺያ ፣ ቦስኒያ እና ሄርዜጎቪና ፣ ሞንቴኔግሮ ፣ አልባኒያ ፣ ግሪክ ፣ ቱርክ ፣ ቆጵሮስ
- እስያ ፦ ቱርክ ፣ ሶርያ ፣ ሊባኖስ ፣ እስራኤል ፣ ጋዛ ፣ ግብፅ
- አፍሪካ ፦ ግብፅ ፣ ሊቢያ ፣ ቱኒዚያ ፣ አልጄሪያ ፣ ሞሮኮ