መንዝ የሚለው ስያሜ የመጣው ከግዕዝ ቃል ሲሆን ትርጉሙና አመጣጡም መንዛት መርጨት ከሚለው ቃል የመጣ ሲኾን ሊቀ መልዐክቱ ቅዱስ ዑራኤል የጌታችንን ደም የረጨባት የምድር ማእከል ናት ፡፡

መንዝ
ጓሳ፣ መንዝ
ከፍታ 2706
የሕዝብ ብዛት
   • አጠቃላይ 39,052
መንዝ is located in ኢትዮጵያ
{{{alt}}}
መንዝ

10°15′ ሰሜን ኬክሮስ እና 39°30′ ምሥራቅ ኬንትሮስ

መንዝ ማለትም ደሙን የረጨበት ስለሆነ ነዝሃ መንዝ ተባለ ፡፡  

ቅዱሱ ጽዋም እዚችው ምድር ሲገኝ ብዙ ምስጢራት ስላላት ከዚህ በላይ መናገር አልችለም ፡፡በጣምም ቅዱስ ስፍራ ነው ፡፡

መንዝ በሰሜናዊ ሸዋ የሚገኝ ክፍል ሲሆን በውስጡ ላሎ ምድርን በስተደቡብ፣ ጌራ ምድርን በስተሰሜንና ማማ ምድርን በመካከል ይዞ ይገኛል[1] ። የመንዝ ድንበር በ3 ወንዞችና በአንድ ተራራ እንዲህ ይካለላል፦ ሞፋር ወንዝ (ደቡብ)፣ አዳባይ ወንዝወንጭት ወንዝ (ምዕራብ)፣ ቀጨኔ ወንዝ (በሰሜን) እንዲሁም በስተምስራቅ ከቆላው ኤፍራታግድምቀወት የሚለየው የተራራ ሰንሰለት ናቸው [2]

ታሪክና ባህል ለማስተካከል

መንዝ ለመጀመሪያ ጊዜ በታሪክ ተጠቅሶ የሚገኘው በቀዳማዊ አጼ አምደ ጽዮን ዜና መዋዕል ሲሆን በጊዜው መንዝሔል ይባል ነበር [3]። ቀጥሎም በአጼ በእደ ማርያም ዜና መዋዕል ተጠቅሶ ይገኛል [4]

መንዝ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ቁልፍ ቦታ የያዘው በ17ኛው ክፍለ ዘመን መጠናቀቂያ፣ በነጋሲ ክርስቶስ ነበር። የመንዝ ተወላጁ ነጋሲ የአጋንጫ ኪዳነ ምህረትን ቤተክርስቲያን በመመሰረት ሲታወቅ የፍሩክታንም ደብር በማስፋፋት ይጠቀሳል። ነጋሲ ታላቁ እያሱን ለመጠየቅ በሄደበት በትክትክ በሽታ ሲያርፍ ልጁ ሰባስቲያኖስ ሸዋን ከመንዝ ሆኖ ያስተዳድር ነበር። ኋላ ላይ የተነሱት ንጉስ አብይ፣ ምንም እንኳ እናታቸው ከላሎ ምድር የመጣች ብትሆንም መስተዳድራቸውን ከመንዝ ወደ ሐር አምባ በማዛወራቸው የመንዝ ማዕከላዊነት ደበዘዘ። የሆኖ ሆኖ መንዝ ለሚቀጥሉት ዘመናት ታዋቂ መሪወችን በማፍራትና በማስተናገድ ትታወቃለች። ለምሳሌ የነጋሲ ዘር የሆነው መርድ አዝማች አስፋ ወሰን በ18ኛው ክ.ዘመን መጨረሻ ጠላቶቹ ሲያሳድዱት በፍሩክታ ኪዳነ ምህረት እንደተጠለለ ይነገራል። የንጉሥ ሣህለ ሥላሴ እናት ወይዘሮ ዘነበወርቅ፣ የነጋሲ ዘር ሲሆኑ ዋና ከተማቸውን በሰላ ድንጋይላሎ ምድር መሥርተው ይኖሩ ነበር። እንዲሁም አቶ በዛብህ ("አባ ደቅር") የመንዝ ባላባት ሲሆኑ በዓፄ ቴዎድሮስ የአበጋዝ ሹም የነበሩና የአጠቃላይ ሸዋ አስተዳዳሪና ኋላ ላይ ከወደፊቱ ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ ሠራዊት ጋር በአምባ ዳየር ጦርነት አድርገው የተሸነፉ ናቸው። ቆይቶም ዓፄ ምንሊክ በአምባ አፍቃራ፣ መንዝ፣ ቤተ መንግሥትና የጦር መሣሪያ ግምጃ ቤት ገንብተዋል። በኋላ በጣሊያን ወረራ ወቅት ለነበረው ትግል መንዝ ማዕከላዊ ሚናን ተጫውቷል።

ባህላዊ መልክዓ ምድር ለማስተካከል

መንዝ እጅግ ለም የሆነ መሬት የሚገኝበት ሲሆን ጥሩ ዝናብ ሲገኝ በአመት እስከ 3 ጊዜ እህል ማጨድ ይቻላል። የአየር ጸባዩም፣ ከከፍታው አንጻር ደጋማ ሲሆን በደቡቡ ማማ ምድር የሚገኘው የአየር ንብረት ወይና ደጋማ ነው። ይህ ሆኖ እያለ የመሬቱ ተራራማ አቀማመጥ ከሞላ ጎደል በዚህ አካባቢ የሚደረግን ግብርና ከባድ ያደርገዋል።

በመንዝ የሚገኙ ቤቶች በባህር ዛፍ እና ጥድ የሚታጀቡ ሲሆን አቀማመጣቸውም ተሰባጥረው ነው። በሞላሌ የሚገኘው የቅዳሜ ገበያ እስከ 2000 ሰወችን ያስተናግዳል።

ከከፍታው አንጻር፣ ብዙው የመንዝ አካባቢ ብርዳማ ስለሆነ ልብስ የሚሰራው ከሪዝ (wool) ነው። ይህም ልብስ ባና ይባላል። እንጀራም ብዙ ጊዜ ከገብስ የሚጋገር ሲሆን የመንዝ ሰወች ውርጩንና ንፋሱን ለመከላከል ቤቶቻቸውን ከእንጨትና ጭቃ ይልቅ ከድንጋይ መሰራት ያዘወትራሉ። ከዚህ እና መሰል ባህላዊ ቅርሶች አንጻር በአካባቢው ሕዝብ ዘንድ መንዝ «የአማራ ምንጭ» በመባል ይታወቃል።

ክርስትና ለማስተካከል

በኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንና ደብር ስብጥር የሚገኘው በመንዝ ነው። ቅዱስ ዮሐንስ ምስራቃዊ ( የመንዝ ሃዋርያ) ለአካባቢው ህዝብ ክርስትናን እንደሰበከ ትውፊት አለ። እንደ ታሪክ ተመራማሪወች አባባል ይህ ሰው በአጼ አምደ ጽዮን ዘመን የነበረው ዮሐንስ ዘቀላት ሲሆን በአቡነ ያቆብና የደብረ ሊባኖሱ እጨጌ ፍሊጶስ ታዞ በ1322 ዓ.ም. ይተጋ የነበረ ሓዋርያ ነው።

አብያተ ክርስቲያናት ለማስተካከል

ጓሳ ሜዳ ለማስተካከል

 
ቀይ ተኩላ፣ ጓሳ፣ መንዝ

የጓሳ ሜዳ በመንዝ የሚገኝ፣ወደ 110 ኪሎ ሜተር ስኩየር የሚጠጋ ስፋት ያለው፣ ከኢትዮጵያም ሆነ አፍሪካ ትልቁ የአፍሮ አልፓይን ስርዓተ ህይወት ቅሪት ነው። በዚህ ሜዳ 26 ምንጮች ሲኖሩ ቦታው ሳይታረስ ለ400 አመታት የተለያዩ ብርቅ እንስሳት (ምሳሌ፡- ጭላዳ ዝንጀሮ (200 የሚጠጉ) ፣ ቀይ ቀበሮ (ከ20 እስከ 50 ብቻ የሚደርሱ) ፣ አጋዘን፣ ወዘተ...) መኖሪያ በመሆን አገልግሏል። የአካባቢው ሕዝብ የዚህን ጉዳይ መሰረት ሲያስረዱ፣ ከላይ የተጠቀሰው ጻዲቁ ዮሐንስ ምስራቃዊ በዚህ አካባቢ ሲኖር ሳለ አንዲት ሴት በውሸት አስረግዞኛል ብላ ከሰሰችው። የአካባቢውም ሕዝብ ይህን ክስ ከጻዲቁ ፊት እንድትደግም አደረጓት እርሷ ግን ክሱን መድገም ብቻ አይደለም "ከዋሸሁ ድንጋይ ያድርገኝ" ብላም ጨመረች። በዚህ መሰረት ንግግሯን ሳታቋርጥ ወደ ድንጋይ ተቀየረች። ጻዲቁም በማዘን ሜዳው ምንም እህል እንዳያበቅል ተራገመ። በዚህ መሰረት በጥሩ ጤፍ ምርቱ ይታወቅ የነበረው ጓሳ የተለያዩ አውሬዎች መኖሪያ ኾነ።

በአኹኑ ወቅት በጓሳ ሜዳ 7 ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ የሚገኙ አጥቢ እንስሳት ይገኛሉ - ይህም ከአጠቃላዩ ኢትዮጵያ ብቻ ከሚገኙት አጥቢ እንስሳት 22.6% ነው። 111 የወፍ አይነቶች በመንዝ ሲገኙ ሰባቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ የሚገኙ ናቸው።

ማጣቀሻ ለማስተካከል

  1. ^ Donald N. Levine, Wax and Gold: Tradition and Innovation in Ethiopia Culture (Chicago: University Press, 1972), p. 28
  2. ^ Levine, Wax and Gold, p. 289 n. 13
  3. ^ G.W.B. Huntingford, The Historical Geography of Ethiopia (London: The British Academy, 1989), p. 80
  4. ^
     
    የአጼ በእደ ማርያም ዜና መዋዕል፣ ገጽ 201