ሐቱሳሽ
(ከሐቱሳስ የተዛወረ)
ሐቱሳሽ ወይንም ሐቱሻ፣ ሐቱሽ በጥንታዊ ሐቲ (አናቶሊያ) የነበረ ከተማ ሲሆን አሁን በቱርክ አገር ያለው ፍርስራሽ ነው። ይህ የሐቲ ዋና ከተማ ነበረ። የአሦር ሰዎች ካሩም (የንግድ ጣቢያ) መሠረቱበት። በኋላ የካነሽ ንጉሥ አኒታ የሐቲ ንጉሥ ፒዩሽቲን አሸነፈ፤ ከተማውንም አፈረሰ፣ ፌጦ ዘራበት፣ ዳግመና የሚሠፍርበትን ንጉሥ ሁሉ ረገመ። ቢሆንም ከመቶ ያህል አመታት በኋላ የኩሻራ ሰው 1 ሐቱሺሊ እንደገና ሠፈረው፤ ሐቱሻም ሁለተኛ ዋና ከተማ ሆነ። ይህም የኬጥያውያን መንግሥት መሠረት ነበረ። እስከ ኬጥያውያን ውድቀት (ምናልባት 1180 ዓክልበ. አካባቢ) ድረስ እንደ ዋና ከተማቸው አገለገለ።
ሐቱሳሽ | |
---|---|
የሐቱሻ አናብሥት በር | |
ሥፍራ | |
ዘመናዊ አገር | ቱርክ |
ጥንታዊ አገር | ሐቲ |
በፍርስራሹ ውስጥ የኬትያውያን መዝገቦች እነርሱም 30 ሺህ ያህል የኩነይፎርም ጽላቶች በኬጥኛ ተጽፈው ተገኝተዋል።