ከ«ትሪቶን» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
አዲስ ገጽ ፈጠረ፦ «'''ትሪቶን''' (ግሪክ (ቋንቋ)፦ Τρίτων) በግሪክ (አገር) አረመኔ ሃይማኖትአፈ ታሪክ ዘንድ...»
(No difference)

እትም በ23:50, 20 ኦገስት 2011

ትሪቶን (ግሪክ፦ Τρίτων) በግሪክ አረመኔ ሃይማኖትአፈ ታሪክ ዘንድ፣ የውቅያኖስ መልእክተኛ የሆነ አምልካ ነበረ። የፖሰይዶን (የባሕሮች ዋና አምላክ) እና የአምፊትሪቴ ልጅ ይባላል። በትውፊቶቹ እንደሚገለጽ፣ ሰውነቱ ከሆዱ በታች የዓሣ ሲሆን፣ ልዩ የዛጎል ቀንድ ይነፋል።

በአንዳንድ የግሪክ ደራሲ እንደ ፒንዳርሄሮዶቱስአፖሎኒዮስ ሮዲዮስሉኮፍሮንዲዮዶሮስ ሲኩሉስ ዘንድ፣ ትሪቶን የሊብያ ንጉሥ ሲሆን መኖርያው በትሪቶኒስ ሀይቅ አጠገብ ተገኘ። በዚሁ ሚና ያሶንና አርጎናውቶች በሚልባለው አፈታሪክ ይጫወታል።

ጣልያናዊ መኖኩሴ አኒዩስ ዴ ቪቴርቦ ባሳተመው ዜና መዋዕል ዘንድ (1490 ዓ.ም. የታተመ)፣ ትሪቶን ከካም ልጆች አንዱ ሲሆን በናምሩድ 18ኛው አመት በሊብያ ሠፈረና መጀመርያው የሊብያ ንጉሥ ሆነ፤ ከዚያ በቤሉስ 56ኛው አመት ያኑስ ወደ ሊብያ ደረሰና የትሪቶን ልጅ ሃሞን ተከተለው። በዚህ ዜና መዋዕል አቆጣጠር ትሪቶን በሊብያ የነገሠ ምናልባት ከ2410 እስከ 2315 ዓክልበ. ግድም ነበር።