ትሪቶኒስ ሀይቅ
ትሪቶኒስ ሀይቅ በጥንታዊ ግሪክ አፈ ታሪክ ውስጥ በሊብያ የተገኘ ታላቅ ሐይቅ ነበረ። ብዙ የግሪክ ሃይማኖት አማልክት እንደ ትሪቶን፣ ሃሞን፣ ፓላስ፣ አቴና፣ ዲዮኒስዮስና ክሮኖስ ከዚህ አካባቢ ጋር ግንኙነት ነበራቸው።
ሄሮዶቱስ፣ ዲዮዶሮስ ሲኩሉስና ሌሎች እንዳሉት፣ ይህ ሀይቅ ከቀርታግና ደቡብ በዛሬው ቱኒዚያ ይገኝ ነበር። ከዚህ ጋር «ትሪቶን» የሚባል ወንዝ ይፈስበት ነበር። በሄሮዶቱስ ዘንድ ሁለት ደሴቶች እነርሱም ፍላ እና ሜኔ አሉበት። ዲዮዶሮስ እንዳለው ኒሳ ደሴት በትሪቶን ወንዝ ውስጥ ነበረ፤ ሄሮዶቱስ ግን ኒሳ በአይቲዮፒያ በተገኘ ሀይቅ ላይ መኖሩን መሰከረ።
ከምድር መንቀጥቀጥ የተነሣ ሐይቁ በግማሽ ወራት ደርቆ አሁን በቱኒዚያ አገር በበጋ የሚሞላ በክረምትም የሚደረቀው ሐይቅ ሻት አል-ጀሪድ እንደ ሆነ ይታሥባል።