ልውውጠ ሰብል
ልውውጠ ሰብል በግብርና ማለት ልዩ ልዩ ምርቶች በተከታታይ ወራቶች በልዩ ልዩ እርሻዎች የማዛወር ዘዴ ነው። አንድ ሰብል በአንዱ እርሻ በየዓመቱ ከመተክል ይልቅ የልውውጠ ሰብል ዘዴ ለመሬቱ (ላይ አፈር) እንዳይደክምበት እጅግ ይሻላል።
በአውሮፓ ከ800 ዓ.ም. በፊት የሁለት እርሻ ልውውጠ ሰብል በሰፊ ይጠቀም ነበር። በዚህ ዘዴ ግማሹ መሬት በአንድ አመት ሲተክል ሌላው ግማሽ አርፎ አደር ይቀራል። በሚከተለውም አመት ይገለበጡ ነበር።
ከ800 ዓ.ም. በኋላ የሦስት እርሻ ልውውጠ ሰብል ይስፋፋ ጀመር። አንዱ እርሻ በስንዴ፣ ሁለተኛውም በአተር ምስር ወይም ባቄላ፣ ሦስተኛውም አርፎ አደር ቀረ። በሚከተለው አመት የእርሻ ሚናዎች ተለዋወጡ። አተር ምስርና ባቄላ በተለይ ለአፈሩም ሆነ ለሰዎች የተሻለ ምግብ ይሰጣሉ። ስንዴ የአፈር ናይትሮጅን ሲፈጅ፣ ባቄላ ግን ናይትሮጅን ይመልሰዋል።
ከ1500 እስከ 1900 ዓ.ም. ድረስ በአውሮፓ ገበሬዎች የ3 እርሻ ልውውጠ ሰብል ሲጠቀሙ በአንዱ እርሻ ስንዴ፣ በአንዱም ገብስ ወይም ኣጃ፣ ሦስተኛውም አርፎ አደር ይለዋወጡ ነበር። በዚህ ዘመን ደግሞ የአራት እርሻ ልውውጠ ሰብል ይስፋፋ ጀመር። በዚህ ዘዴ አራቱ ሰብሎች ይለዋወጣሉ፣ እነርሱም ስንዴ ዱባ ገብስና ሣር (ለመኖ) የሚመስል ናቸው። ይህ ለግብርና ዘዴ ለምርት ትልቅ ማሻሻል ሆነ።