ሃይል (ፊዚክስ)
- «ሃይል» የሚለው አርዕስት ወዲህ ይመራል። ተጨማሪ ትርጉሞችን ለማየት፣ ኃይልን ይመልከቱ።
ሃይል በተፈጥሮ ህግጋት ጥናት ሲተረጎም ስራ የሚሰራበት ፍጥነት ማለት ነው። በሌላ አነጋገር ሃይል ማለት አቅም ካንድ ቁስ ወደሌላ የሚተላለፍበት ፍጥነት ወይም ደግሞ አንድ አይነት አቅም ወደ ሌላ አይነት የሚቀየርበት ፍጥነት ማለት ነው። የሃይል መለኪያ መስፈርት ዋት (w) ነው።
በሃይልና አቅም ልዩነት አለ። ለምሳሌ አንድን ድንጋይ ከመሬት ወደተወሰነ ቦታ ለማንሳት (በፍጥነትም ይሁን በዝግታ) የሚጠይቀን አንድ አይነት አቅም ነው። ነገር ግን ድንጋዩን በፍጥነት ማንሳት እና ዝግ ብሎ ማንሳት የተለያየ ኃይልን ይጠይቃል። በፍጥነት ለማንሳት ከፍተኛ ሃይል ሲጠይቅ ዝግ ብሎ ለማንሳት ግን ዝቅተኛ ይጠይቃል። በሌላ አነጋገር፣ ብዙ አቅም ካለ ብዙ ስራ መስራት ይቻላል፤ ብዙ ሃይል ካለ ደግሞ ብዙ ስራን በትንሽ ጊዜ መጨረስ ይችላል።
ሃይል እንደ ስራ ውድርነቱ መጠን ቀመሩ ይህን ይመስላል፦
አጠቃላይ ሃይል
ለማስተካከልእዚህ ላይ