ኃይል
ኃይል የተለያዩ ትርጉሞች አሉት። በጠቅላላው «ለውጥ የማስካሂድ ማንኛውም ችሎታ» ማለት ነው።
- በፊዚክስ፦ ሃይል (ፊዚክስ) ማለት በተወሰነ ጊዜ ምን ያህል ሥራ እንደሚፈጸም (ምን ያህል ጉልበት ወደ ሥራ እንደሚቀየር) የሚያመልከት ቁጥር ነው። የዚህ ኅይል መስፈርያ ዋት ይባላል።
- የመብራት ኃይል ወይም ኤሌክትሪክ - ይህ አይነት ኃይል ከኃይል ማመንጫ ጣቢያ የሚፈጠር ነው።
- በሰው ልጅ ጥናት፣ ኃይል ማለት አንድ ሰው በሌላ ሰው ላይ ያለው ተጽዕኖ ወይም ሥልጣን ማለት ነው።
- በፖለቲከ ረገድ፣ ኃይል ማለት አንድ ሀገር ሌላውን የሚያስገድድበት ጉልበት ነው። ይህ አይነት ኃይል ከሠራዊቱ ወይም ከሀብቱ ብዛት የሚወጣ ሊሆን ይችላል።
- በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የእግዚአብሔር ኃይል ወይም ሥልጣን በብዛት ይጠቀሣል። ለምሳሌ መክብብ 8፡8፣ 1 ሳም. 2፡4፣ መዝሙር 61፡11።