ሕምያር
(ከሂምያር የተዛወረ)
ሕምያር ከቀይ ባሕር በስተምሥራቅ ላይ የነበረ ሕዝብ ነው። የሕምያር ስም የንጉሥ ኢዛና የማዕረግ ስም ውስጥ ተካትቶ በአክሱም የድንጋይ ጽሑፎች ውስጥ ይገኛል። በግዕዝ የድንጋይ ላይ ጽሑፎች ውስጥ ሐመየረ ፣ ሐመረ ፣ ሕሜር ፣ ሐሜር ተብሎ ተጽፎ እናገኘዋለን። በጥንታዊት ኢትዮጵያ ታሪክ ጥናት ውስጥ ትልቅ ቦታ ካላቸው ስፍራዎች መካከል አንዱ ነው።
ከ372 እስከ 517 ዓም. ድረስ የሕምያር መንግሥት በየመን ውስጥ ተመሠርቶ በይፋ የመንግሥት ሃይማኖት አይሁድና (ብሉይ ኪዳን) ሆነ።