«የተከሠተው ዕድል»
«የተከሠተው ዕድል» ማለት የአሜሪካ መንግሥት ግዛት ከአትላንቲክ ውቅያኖስ ጀምሮ እስከ ሰላማዊው ውቅያኖስ ድረስ መስፋፋቱ ልዩ ዕድል እንደ ነበር የሚል እምነት ነው።
አንዳንዴም የተከሠተው እድል ደግሞ ስሜን አሜሪካ በሙሉ ከነካናዳ፣ ሜክሲኮ፣ ኩባና መካከለኛው አሜሪካ ጋራ ሁሉ እስከሚመጠት ድረስ የሚል ሰፊ ትርጉም ተሰጠው። ከዚህ በላይ ይኸው ፅንሰ ሀሣብ ሌሎችን ግዛቶች መግዛቱን ለማጽደቅ ተጠቅሞ ያውቃል። በተከሠተው ዕድል አራማጆች አስተያየት ዘንድ መስፋፋቱ ጥሩ ነገር ከመሆኑ በላይ ግልጽ (የተከሠተው) እና እርግጥኛ (ዕድል) ነው ብለው አመኑ። በመጀመርያ ዘይቤው የ19ኛው ክፍለ ዘመን ፖሊቲካዊ መፈክር ሆኖ በጊዜ ላይ ለአሜሪካ መንግሥት በአሕጉሩ ዳር እስከ ዳር መስፋፋት ተራ ታሪካዊ መግለጫ ሆነ።
ዘይቤው መጀመርያ በተለይ በጃክሶኒያን ዴሞክራት ወገን በ1840ዎቹ አሁን ምዕራብ አሜሪካ ያለውን ማለት ኦሬጎን ግዛት፣ ቴክሳስ ሬፑብሊክና በዚያን ጊዜ ስሜን ሜክሲኮ የነበረውን በኃይል መያዙን ለመምዋገት ይጠቀም ነበር። ሁለተኛ በ1890ዎቹ በሪፐብሊካን ወገን ደጋፊዎች መሃል አሜሪካ አገር ከስሜን አሜሪካ ውጭ እንድትስፋፋ የሚያጸድቅ ሃልዮ እንዲሆን ተነሣ።
በ20ኛ ክፍለ ዘመን ዘይቤው በአሜሪካ መሪዎች ዘንድ ቶሎ ከጥቅም ወደቀ፣ ዳሩ ግን አንዳንድ ተቺዎች እንደሚያምኑ፣ ልዩ ልዩ የተከሠተው እድል ረገዶች፣ በተለይም በዓለም ዙሪያ ዴሞክራሲ ለመግፋፋትና ለመከላከል ያለው አሜሪካዊ 'ተልዕኮ' የመኖሩ እምነት፣ እስካሁን በአሜሪካ ፖሊቲካዊ ርዕዮተ ዓለም ላይ ተጽእኖ አሳድሮአል ይላሉ።