ማይክሮሶፍት
(ከMicrosoft የተዛወረ)
ማይክሮሶፍት ኮርፖሬሽን ዓለም-አቀፍ የቴክኖሎጂ ድርጅት ነው። እንደ ጁላይ 2006 እ.ኤ.አ. ማይክሮሶፍት 71,553 ሠራተኞች በ102 ሀገሮች ሲኖረው፣ ዓመታዊ ገቢው 44.28 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ነው። እጅግ በጣም ብዙ የሚሆኑ ሶፍትዌሮችን ማምረትና ማዳበር ዋና ዓላማው ነው። ዋና መስሪያቤቱ በሬድመንድ፣ ዋሽንግተን፣ አሜሪካ የሚገኝ ሲሆን፣ ታዋቂ ምርቶቹ ማይክሮሶፍት ዊንዶውስ ስርአተ ክወና እና ማይክርሶፍት ኦፊስ ግሴት ሶፍትዌር ያጠቃልላሉ። ከሶፍትዌሮች ሌላ፥ ኤም.ኤስ.ኤን.ቢ.ሲ የኬብል ቴሌቪዥን፥ ኤም.ኤስ.ኤን. ዌብሳይት፥ ማይክሮሶፍት ኢንካርታ የኢንተርኔት መዝገበ ዕውቀት፥ የቤት መዝናኛ እና ሌሎችም ምርቶችና አገልግሎቶችን ያቀርባል።
Microsoft Corp. | www.microsoft.com | |||
---|---|---|---|---|
150px| | ||||
ኢንዱስትሪ | ኮምፒዩተር ሶፍትዌር ኮምፒዩተር ሐርድዌር ቴሌቪዥን ምርምርና ማዳበር ኢንተርኔት | |||
ዓይነት | የሕዝብ | |||
የምስረታ_ቦታ | አልበከርኪ፥ ኒው ሜክሲኮ (April 4,1975 እ.ኤ.አ.) | |||
ዋና_መሥሪያ_ቤት | ሬድመንድ፥ ዋሽንግተን፥ አሜሪካ | |||
ቁልፍ_ሰዎች | ቢል ጌትስ፥ መሥራችና ዳይሬክተር ፖል አለን፥ መሥራች | |||
ምርቶች | ዊንድዎስ ኦፊስ ሰርቨርስ ስካይፕ ቪዥዋል እስቲድዮ ዳይናሚክስ አዡር ኤክስ ቦክስ ሰርፌስ | |||
ገቢ | $44.28 ቢሊዮን (2006 እ.ኤ.አ.) | |||
የተጣራ_ገቢ | $44.28 ቢሊዮን (2006 እ.ኤ.አ.) | |||
የሰራተኞች_ብዛት | 114,000 (በሰኔ 30 2016 እ.ኤ.አ.) |