1 ዚዳንታ በ1491 ዓክልበ. አካባቢ ከንግሥቱ አባት ከ1 ሐንቲሊ በኋላ በሐቱሳሽ (በሐቲ አገር ወይም የኬጥያውያን መንግሥት) የገዛ ንጉሥ ነበር።

የዚዳንታ ንግሥት ስም በሙሉ አልተገኘም፣ በ -ሻ ወይም -ታ እንደ ጨረሰ ሊነብብ ይቻላል። አባቷም ሐንቲሊ ገና የ1 ሙርሲሊ «የዋንጫ ተሽካሚ» እየሆነ፣ በ1507 ዓክልበ. ገደማ፣ በዚዳንታ ምክር ሐንቲሊ በሙርሲሊ ላይ መንፈቅለ መንግሥት ሠርቶ ንጉሥነቱን ያዘበት።

ይህን የምናውቀው ሁሉ ንጉሡ ቴሌፒኑ በጻፈው የቴሌፒኑ ዐዋጅ በተባለው ሰነድ የሐንቲሊ ዘመን ይተረካል። ከዚያም ዚዳንታ የሐንቲሊን ወራሾች ገድሎ ዚዳንታ በሐቲ ዙፋን ላይ ተከተለው። በአጭር ጊዜ ውስጥ ግን ዚዳንታ በገዛ ልጁ አሙና ተገደለ፤ አሙናም የኬጥያውያን ንጉሥ ሆነ።

«ሐንቲሊ ባረጀ ጊዜ እሱም አምላክ ሊሆን ሲል [በኬጥኛ ዘይቤ ለንጉሣቸው ብቻ ተብሎ ሊያርፍ ሲል ማለት ነው]፣ ዚዳንታ የሐንቲሊን ልጅ ፒሼኒን ከነልጆቹም ከነሎሌዎቹም ገደላቸው።
ዚዳንታም ንጉሥ ሆነ። አማልክት ስለ ፒሼኒ ደም ቂም ፈለጉ። አማልክት የገዛ ልጁ አሙና እንደ ጠላቱ አድርገው እሱም አባቱን ዚዳንታን ገደለ።»

ከዚሁ ሰነድ በቀር ስለ ዚዳንታ የሚነግረን አንዳች ሌላ ቅርስ ስላልተገኘ ቶሎ እንዳለፈ ይሆናል።

ቀዳሚው
1 ሐንቲሊ
ሐቲ ንጉሥ
1491 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
አሙና