1995
(ከ፲፱፻፺፭ የተዛወረ)
1995 አመተ ምኅረት
- ነሐሴ 19 ቀን - 52 ሰዎች በሙምባይ ህንደኬ በእስላም ታጣቂዎች ቦምብ ተገደሉ።
- ኅዳር 6 ቀን - በቻይና ሕዝባዊ ሪፑብሊክ ሁ ጂንታው የኮሙኒስት ቡድን መሪ ሆኑ።
- ኅዳር 12 ቀን - «የሰሜን አትላንቲክ ስምምነት ድርጅት» (ኔቶ - NATO) ሰባት የቀድሞው የ«ምሥራቃዊ ኃይል» አባላት አገሮችን ለድርጅቱ አባልነት ጋበዛቸው። የተጋበዙት አገሮች፦ ቡልጋሪያ፣ ኤስቶኒያ፣ላትቪያ፣ ሊቱዌኒያ፣ ሩማንያ፣ ስሎቫኪያ እና ስሎቬኒያ ናቸው።
- ኅዳር 13 ቀን - በናይጄሪያ በወቅቱ ሊካሄድ በታቀደው ከ«ወይዘሪት ዓለም» የቁንጅና ውድድር ጋር በተያያዘ ጉርምርምታ መነሻነት «ThisDay» በተባለ የናይጄሪያ ጋዜጣ ላይ የወጣው ‘ሐይማኖት ነክ’ አንቀጽ ባስከተለው ሽብር ከሁለት መቶ በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ። ውድድሩም በዚሁ ሽብር ምክንያት ወደ ለንደን ተዛወረ።[1]
- ሐምሌ 1 ቀን - አንድ መቶ አሥራ ስድስት መንገደኞችን የጫነው የሱዳን አየር መንገድ (Boeing 737-200) አውሮፕላን ፖርት ሱዳን በአደጋ ሲከሰከስ አንድም የተረፈ ሰው አልነበረም።
ክፍለ ዘመናት፦ | 19ኛ ምዕተ ዓመት - 20ኛ ምዕተ ዓመት - 21ኛ ምዕተ ዓመት |
አሥርታት፦ | 1960ዎቹ 1970ዎቹ 1980ዎቹ - 1990ዎቹ - 2000ዎቹ 2010ሮቹ 2020ዎቹ
|
ዓመታት፦ | 1992 1993 1994 - 1995 - 1996 1997 1998 |
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |