ኢንጂኔር ፍሥሓ አጥላው /Fesseha Atlaw (ፍስሐ አጥላው፤ ፍስሀ አጥላው )ግዕዝ ኢትዮጲክ /ETHIOPIC ፊደል ሶፍትዌር እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ1980 ዎቹ ሊቅ ናቸው። ኢንጂኔር ፍሥሓ አጥላው በኢትዮጵያና በመላው ዓለም የሚታወቁት የኢትዮጵያን ፊደላት ለመጀመሪያ ጊዜ ከኮምፒውተር አዛምደው ፤ የመጀመሪያውን የአማርኛ የኮምፒውተር ቃላት ማቀነባበሪያ ( Amharic Word Processor) ፕሮግራም ለተጠቃሚዎች በማቅረባቸው ነው•.

ፍሥሓ አጥላው (Fesseha Atlaw) ከአባታቸው ከአቶ አጥላው ወልደዮሐንስ እና ከእናታቸው ወይዘሮ ሐመረ ገብረፃድቅ በአዲስ አበባ ከተማ 1955 ዓም ተወለዱ።  ለ12 አመታት ትምህርታቸውን የተከታተሉት በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ አንደኛ ደረጃ ተመላላሽ /ኮከበ ፅባህ ትምህርት ቤት ነበር። ገና የአንደኛ ክፍል ሕፃን ተማሪ በነበሩበት ጊዜ ባስገኙት ልዩ የትምህርት ውጤት ተመርጠው ፤  ከንጉሰ ነገስቱ ፤ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ እጅ ወደ ቤተ መንግስት ተልከው ልዩ ሽልማት ተቀብለዋል ።  አንደኛ ና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁት በዚሁ አሁን ኮከበ ፀባህ ተብሎ በሚጠራው ትምህርት ቤት ነው ። 

በዚህ ትምህርት ቤት ሳሉ ከመደበኛ ትምሄርቶች ውጬ በልዩ ልዩ ከለቦችና የትርፍ ጊዜ እንቅስቃሴዎች ይካፈሉ ነበር ። ለምሳሌ ለመጥቀስ ፤ የሙዚቃ ባንድ ፤ የወጣት ደራሲያን ክለብ ፤ የመፅሐፍ ቅዱስ ከለብ ፤ የሬዲዮና ጋዜጣ ክለብ ይገኙበታል ። ዘጠነኛ ክፍል ሳሉ በአዲስ አበባ በተደረገ የአሜሪካን የቴክኖሎጂ ኤክዚቢሽን አዘጋጆች የፍሥሐ አጥላውን የዘጠነኛ ክፍልን መርጠው ወደ አዳራሹ በአውቶቢስ በመውሰድ የአሜሪካን ቴክኖሎጂ በኢትዮጵያ ወጣቶች ዓይን በሚል ዶኪሜንታሪ ፊልም ተሰርቶ በዓለም ዙርያ ከታየ በኋላ በአሜሪካን ስቴት ዲፓርትሜንት መዝገብ ቤት ይገኛል ። በዚህም ፊልም ወጣቱ ፍሥሐ አጥላው በተደጋጋሚ ከመታየቱም በላይ ፤ ከእንግሊዝኛ አስተማሪው፤ ከወይዘሮ ብርሃኔ አስፋው ጋር ያደረገው ጥያቄና መልስም ተቀድቶ የዚህ ታሪካዊ ፊልም አካል ሆኖ ይታያል ። ፊልሙ አሁን ዩ ቲውብ ላይ “ Fesseha Atlaw USA, Ethiopia “ በሚል ማጣቀሽያ ርዕስ ይገኛል ። ቀጥሎም በአዲስ አበባ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርስቲ ገብተው ፤ በኢንጅኔርንግ መስክ ትምህርታቸውን መከታተል ሲጀምሩ ፤ በተማሪዎች የፖለቲካ እንቅስቃሴ በተነሳ ግጭት ዩኒቨርስቲው ስለተዘጋ ፤ ከኢትዮጵያ ወጥተው ትምህርታቸውን ለመከታተል አውሮፓና አሜሪካን አገር ካሉ ዩኒቨርስቲዎች ጋር መፃፃፍ ጀመሩ ። ብዙዎች ዩኒቨርቲዎች ቢቀበሏቸውም ሙሉ (100%) ስኮላርሺፕ ሰጥቶ የተቀበላቸው ኦክላሆማ የሚገኘው ኦራል ሮቤርትስ የተባለው ዩኒቨርስቲ ነበር ። ከዚሁ ዩነቨርስቲ በ ቴሌኮሙኒኬሽንና በ ማቲማቲክስ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በ1975 ተቀብለው፤ ለሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪያቸው ወደ ዩኒቨርስቲ ኦፍ ኔብራስካ አመሩ ፤ የባዮ ሜዲካል ቴሌኮሙኒኬሽን፤ ሲስቴም ኤንጅኔርንግ እንዲሁም በአፕላይድ ማቲማቲክስ ፤ ሁለት የማስተርስ ዲግሪ በ1978 አጠናቀው ፤ ከአሜሪካን መንግስት በተሰጠ ልዩ ቪዛ ወደ ሥራ መስክ ተሰማሩ ፤ የተቀጠሩበት መሥራያ ቤት ለአሜሪካን ሥራ ሚኒስቴር (Department of Labor) አመልክቶ የመኖሪያ ፈቃድ አግኝቶላችው በሥራ እንዲቀጥሉ ተደረገ ። በሥራ ዓለም ተቀጥረው የሰሩባቸው ሙያዎችና መሥሪያ ቤቶች ፡ 1ኛ FMC Corporation Automated Manufacturing Machine Programming (Robotics) 2) ATARI : Manufacturing Engineering; Game console and personal Computers 3) Hewlett- Packard - Development Engineer/ScientistElectronic Power Conversion Systems 4) Agilent Technologies : Engineering Manager ; Microwave Test Instrumentation 5) Medtronic inc : Research and Development - Bio-Medical Devices Materials በግላቸውና በትርፍ ጊዜያቸው ፡ 1 ) Dashen Engineering Company - Founder and CEO እራሳቸው ባቋቋሙት ዳሽን ኢንጅነሪንግ ኩባንያ አማካይነት የመጀመሪያውን የአማርኛ ኮምፒውተር መፃፊያን ያስተዋወቁ ፈር ቀዳጅ ናቸው። 2 ) Ethiopian Famine Relieve Organization - Chairman በ 1984 በኢትዮጵያ ለይ በደረሰው የድርቅና የረሃብ አደጋ አሜሪካን ያሉ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና ፤ አሜሪካውያንን ያስተባበረ ማኅበር ሊቀ መንበር ሆነው ፤ ወደኢትዮጵያ ገነዘብና ቁሳቁስ በመላክ ፤ የውሃ ጉድጓድም በማስቆፈር ትልቅ አስተዋፅዖ አድርገዋል 3) Unicode Technical Symposium - Life time memberበዓለም ዙርያ የሚገኙ ቋንቋና ፊደላትን በኮምፕውተር ውስጥ ለማካተት በተቋቋመው ዩኒኮድ (UNICODE) የሚባለው የአለም አቀፍ ስታንዳርድ ድርጅት (Internation Standards Organization -ISO ) ሥር በተቋቋመው ኮሚቴ ፤ ኢንጂኔር ፍሥሓ ከመስራች አባላት አንዱ ነበሩ ፤ (የዚህ ኮሚቴ ዋና ዋና አባላት Google ; IBM ; Apple : Amazon ; HP ; Adobe ያካተተ ነበር ። በዚህም ኮሚቴ አማካኝነት ኢንጂኔር ፍሥሓ የኢትዮጵያ ፊደላት ፤ ኢትዮፒክ Ethiopic) በመባል በዓለም ዙርያ የሚፈበረኩ ማንኛውም ኮምፒውተር ውስጥ ቋሚ ቦታ እንዲያዝላችው ትልቁን አስተዋፀዖ አድርገዋል ። 4 ) Director : Fesseha Atlaw Wolde Yohannes Foundation Endowment በ2020 ላይ በቤተሰባችው ስም ባቋቋሙት የበጎ አድራጎት ድርጅት ሥራ ላይ ልዩ ልዩ እርዳታን ኢትዮጵያ ውስጥ ያደርጋሉ ። ከእነዚህም ፡ የጎዳና ተዳዳሪ ወጣት እናቶችንና ልጆቻቸውን እየሰበሰቡ የሚረዳ ድርጅትን መደገፍ በኢትዮጵያ ፊደላት የሞባይል ወይንም የኮምፒውተር መተግበሪያ የሚሰሩ ወጣቶችን ለማበረታታት በየዓመቱ ውድድር በማዘጋጀት ይገንዘብ ሽልማት መስጠት የተለያዩ የኦኮኖሚ ችግር የደረሰባቸውን ወጣት ተማሪዎችንና ሌሎችም የተችገሩ የኢትዮጵያ ዜጋዎች የሚረዱ ድርጅቶችን መርዳት ። ይገኙባችዋል ። ፍሥሓ ከምህንድስና ሙያቸው ባሻገር የደራሲነት ዝንባሌ አላቸው። ገና በ12 አመታቸው መፅሀፍ ፅፈው አሳትመዋል። በ15 አመታቸው ደግሞ የፃፉት ተውኔት በሃገሪቱ ታላቁ ትያትር ቤት በሃገር ፍቅር ለመታየት በቅቷል። ትያትሩ የብዙዎችን ትኩረት ሲስብ ከነሱ መሃል ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ዋነኛው ናቸው። ተውኔቱ ኢትዮጵያን ሔራልድ ላይ "በጣም ምርጥ" ተብሎ ሲሞካሽ የኢትዮጵያ ድምፅ ደግሞ “የ15 ልጅ ቲያትር ደራሲ” በሚል ርዕስ ስለ ተውኔቱ አንድ ሙሉ ገፅ ዘገባና ቃለመጠይቅ አድርጎላቸዋል።

 ኢንጅነሪንግ ለማጥናት ወደ አሜሪካ ሲመጡ የድርሰት ዝንባሌያቸውን ለግዜው ወደ ጎን አስቀምጠውት ነበር ።  የመጀመሪያ ስራቸውን አግኝተው ከተቀጠሩ በኋላ እንደገና ወደ መፃፍ ለመመለስ የአማርኛ ታይፕራይተር አጥብቀው መፈለግ ጀመሩ ። ነገር ግን በደርግ   ዘመን የአማርኛ ታይፕራይተር ማስመጣት የማይታሰብ እና የማይቻል ሆነባቸው። በግዜው ይህንን መሞከር ከባድ ወንጀል ነበር። ብቸኛ የአማርኛ ታይፕራይተር ሰሪዎች ከሆኑት ኦሊቬቲ እና ኦሎምፒያን ጋር ግንኙነት ለመፍጠር ቢሞክሩም አልተሳካላቸውም። ኦሊቬቲ እና ኦሎምፒያ የሚሰሩትን የአማርኛ ታይፕራይተር ከኢትዮጵያ ውጪ ላለመሸጥ ከደርግ የኢትዮጵያ መንግስት ጋር ግዴታ ገብተው ነበር። ምክንያቱም በውጭ ያሉት የመንግስት ተቃዋሚዎች ከሕዝቡ ጋር የሚገናኙት በፅሁፍ ብቻ ሰለነበር ነው (ዴሞክራሲያና የመሳሰሉትም ፀረ መንግስት ፅሁፎች የሚሰሩት ይህንኑ “የአማርኛ የፅሕፈት መኪና” ነበር ። "ችግር ብልሃትን ይወልዳል"  እንደሚባለው ኢንጂኔር ፍሥሓ ለራሳችው ደርሰት መፃፊያ ሲሉ በጊዜው በነበረው የቤት ኮምፒውተር  (Personal Computer) ላይ የመጀመሪያውን  የአማርኛ ቃላት ማቀነባበሪያ ሊፈጥሩ  ተግተው ለመስራት  ወሰኑ።

 በጊዜው ዊንዶውስ ና ማውስ ገና አልተፈጠረም። የቤት ኮምፒውተሮች ገና ዳዴ በማለት እርምጃ ውስጥ ነበሩ። ምንም እንኳን HP የሚሰሩበት HP-150 የተባለ ኮምፒውተር የስራ ዴካቸው ላይም ቢኖር ፤ ከመሥሪያ ቤት ውጭ ገና በጥቅም ላይ ያልዋለና ልዩ የሆነ ሲስትመና ፕሮሴሰር የሚጠቀም ነበር ። በዚያን ጊዜ (በ80 ዎቹ ማለት ነው ) አዳዲስ የቤት ኮምፒውተሮች ወጣ ወጣ ማለት ቢጀምሩም ለመግዝት በጣም ውድ ነበሩ። ኢንጂኔር ፍሥሓ እርካሽ የተባለውን ኮምፒውተር(8086 ፕሮሰሰር) እና ዶት ማትሪክስ ፕሪንተር በ380$ በወር ተከራይተው በግል ጊዜያቸው አማርኛን ከኮምፕውተር ለማዛመድ ጥረታቸውን ጀመሩ። በ1980 በመጀመሪያ ፊደላቱን አንድ ባንድ በእጃቸው በሰንጠረዥ ውስጥ እየቀረፁ ኮምፒውተር ሜሞሪ ላይ ማስገባት ጀመሩ ። ይህም ጊዜ የሚፈጅ ሂደት ከመሆኑም አልፎ የኢትዮጵያ ፊደላት ብዛትና የቅርፆቹም ስፋት በጣም አስቸጋሪ ነበሩ ። ለኮምፒውተር ስክሪንና ለማተሚያ ( Printer)የተለያየ ዲዛይን ያስፈልጋቸው ነበር ፤ የተለያዮ የስክሪን ዓይነቶችና ፤ የማተሚያ ዓይነተች እያንዳንዳቸው የተለያየ ዲዛይን ያስፈልጋቸው ነበር ። ይህንንም ሥራ ለማቅለል ለአማርኛ ተደጋጋሚ የሚመስሉ ፊደላትን ለመቀነስ የመጣላቸውን ሃሳብ ለቋንቋ ምሁራን አማክረው ፤ ፊደሎቹ ለአማርኛ ተደጋጋሚ ቢመስሉም ፤ ለትግርኛ ና ለግዕዝ ልዩ ትርጉም ያላቸው አስፈላጊዎች እንደሆኑ ስለተረዱ የፊደሎቹን የመቀነስ ሃሳብ ትተው እንደውም በጊዜ በነበረው ታይፕ ራይተር ላይ ያልተካተቱ ከአማርኛ ውጭ አዳዲስ ፊደላትን (ለምሳሌ ለትግርኛ “ቐ” የሚለውንና ለፋን ኦሮሞ “ዸ” የሚለውን በማካተት ፊደሎቹ የአማርኛ ብቻ ሳይሆኑ ሁሉንም የኢትዮጵያ ቋንቋዎች የሚወክሉ መሆናቸውን በቋሚ መልክ እንዲቀመጥ አድርገዋቸዋል ። በአለም ዙሪያም የኢትዮጵያ ፊደላት ‘ኢትዮፕክ” በሚባለው ስም የትኛውም ኮምፕውተር ላይ ተጨማሪ ትሮግራም መጬን ሳያስፈልግ ተዘጋጅቶ ለተጠቃሚዎች ቀርቦ ይገኛል ። ስለዚህም ከማንኛውም ቋንቋ ወደ አማርኛ ወይንም ከአማርኛ ወደ እንግሊዝኛ ና ሌሎችም ቋንቋዎች ትርጉሞች ና ፤ በድምፅ የሚያነብና የመሳሰሉ አዳዲስ ቴክኖሎጅዎች ቋንቋችን ተጠቃሚ ሊሆን የቻለው።



የውጭ መያያዣ

ለማስተካከል