ፍሪዩልያን
(ከፍሪኡሊአንኛ የተዛወረ)
ፍሪዩልያን (Furlan) በስሜን-ምሥራቅ እጣልያ በ600,000 ሰዎች የሚናገር ቋንቋ ነው። ከነዚህ ተናጋሪውዎች አብዛኞቹ ደግሞ ጣልኛ የሚችሉ ናቸው። የቋንቋ ስም በጣልኛ ፍሪዩልያኖ ሲሆን በራሱ ግን ፉርላን ወይም ማሪለንጌ ይባላል። ላዲን ለሚባለው ቋንቋ ቅርብ ዝምድና ስላለው አንዳንዴ "ምስራቅ ላዲን" ይሰየማል። ከዚያ በላይ በስዊስ አገር ለሚናገረው ለሮማንሽ ቅርብ ዘመድ ነው።
ዛሬ በጣልያ መንግሥት በኩል ፍሪዩልያን ይፋዊ ሁኔታ አለውና በብዙ ትምህርት ቤቶች ይማራል። ጥቂት ሥነ ጽሑፍ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም፣ ዘፈኖችና አንዳንድ የመንገድ ምልክት፣ ደግሞ የድረ-ገጽ ጋዜጣ በፍሪዩልያን አለ። ባለፈው አመት ውስጥ የቢራ ማስታወቂያ ቢሆንም በፍሪዩልያን በጣልያ ቴሌቪዥን ታይቷል። ስለዚህ ዱሮ ቋንቋው በጣም ትንሽ ከሆነ አሁን ግን በጉልበት እየተመለሠ ነው።
ምሳሌዎች
ለማስተካከል- Mandi, jo o mi clami Jacum!
- ማንዲ፣ ዮ ኦ ሚ ክላሚ ያኩም!
- (ታድያስ፣ ስሜ ያዕቆብ ነው!)
- Vuê al è propite cjalt!
- ቩዌ አል ኤ ፕሮፒቴ ቻልት!
- (ዛሬ አየሩ በጣም ይሞቃል!)
- O scugni propite lâ cumò, ariviodisi.
- ኦ ስኩኚ ፕሮፒቴ ላ ኩሞ፣ አሪቭዮዲሲ።
- (በውኑ አሁን መሄዴ ነው፣ አይሃለሁ።)
- No pues vignî fûr usgnot, o ai di studiâ.
- ኖ ፕወስ ቪኚ ፉር ኡስኞት፣ ኦ አይ ዲ ስቱዲያ።
- ዛሬ ማታ ካንተ ጋር መውጣት አልችልም፣ ማጥናት አለብኝ።