ጣልያንኛ
(ከጣልኛ የተዛወረ)
ጣልያንኛ የጣልያን ሃገር ብሄራዊ የመግባቢያ ቋንቋ ነው። በጣልያን ብቻ 60 ሚሊዮን ዋና ተናጋሪዎች ሲኖሩት በውጭ ሃገር 10 ሚሊዮን ተናጋሪዎች አሉት። በአጠቃላይ 70 ሚሊዮን ዋና ተናጋሪዎች እና ከ125 ሚሊዮን በላይ ሰዎች እንደ የውጭ ቋንቋቸው ይናገሩታል። ለምሳሌ በዋናነት ስዊትዘርላንድ ውስጥ ከሚነገሩ አራት ትልልቅ ቋንቋዎች አንዱ ነው። ቋንቋው በግሪክ፣ ሊቢያ፣ ክሮሽያ እና ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች በጣልያን ቅኝ ግዛት ውስጥ የነበሩ ሃገሮችም ውስጥ ቀላል የማይባሉ ተናጋሪዎች አሉት። በዋና ተናጋሪ ብዛት ከአለማችን 20ኛ ደረጃን ይይዛል።[1]
ዋቢ መጻሕፍት
ለማስተካከል- Berloco, Fabrizio (2018). The Big Book of Italian Verbs: 900 Fully Conjugated Verbs in All Tenses. With IPA Transcription, 2nd Edition. Lengu. ISBN 978-8894034813. https://books.google.it/books?id=DYynDwAAQBAJ&pg=PA1#v=onepage&q&f=false.
- Serianni, Luca; Castelvecchi, Alberto (1997). Italiano. Grammatica, sintassi, dubbi.. Milan: Garzanti.
- Berruto, Gaetano (1987). Sociolinguistica dell'italiano contemporaneo. Roma: Carocci.