ፋይኮሎጂ
ፋይኮሎጂ የሚለው ቃል «የባህር አረም» የሚል ትርጓሜ ካለው (φῦκος) /ፉኮስ/ ከተሰኘ የጥንታዊ ግሪክ ቃል እና «ጥናት» የሚል ትርጓሜ ካለው (-λογία) /ሎጊያ/ ከተሰኘ የግሪክ ቃል ጥምረት የመጣ ሲሆን የዋቅላሚዎች ሳይንሳዊ ጥናት ማለት ነው። አልጎሎጂ በመባልም ይታወቅ የነበር ሲሆን ፋይኮሎጂ የሥነ-ሕይወት ዘርፍ ነው።
ዋቅላሚዎች በውሃ ስነ ምህዳር ውስጥ የመጀመሪያ ደረጃ ምርት በመሆን ያገለግላሉ። አብዛኛዎቹ ዋቅላሚዎች ውን ኑክለሳውያን, የብርሃን አስተጻምሮ የሚያካሂዱ እና እርጥበት ባለበት አካባቢ የሚኖሩ ፍጥረታት ናቸወ። ከከፍተኛ ተክሎች የሚለዩት በእውነተኛ ሥሮች፣ ግንዶች ወይም ቅጠሎች የሌላቸው በመሆኑ ነው። አበቦችን አያብቡም። ብዙ ዝርያዎች ነጠላ-ሕዋስ እና ጥቃቅን (ፋይቶፕላንክተን እና ሌሎች ደቂቅ ዋቅላሚዎችን ጨምሮ) ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ በአንድ ወይም በሌላ ደረጃ ባለብዙ ህዋሳት ናቸው። ከእነዚህ ውስጥ አንዳንዶቹእንደ ከልፕ እና ሳርጋሰም ያሉ የባህር አረሞች ወደ ትልቅ መጠን ያድጋሉ ።
ፋይኮሎጂ ሰማያዊ አረንጓዴአማ ዋቅላሚዎች ወይም ሲያኖባክቴርያ በመባል የሚታወቁትን ቅድመ ኑክለሳውያን ጥናትያካትታል።በርከት ያሉ ጥቃቅን ዋቅላሚዎች እንዲሁ በላይከን ውስጥ እንደ ተደጋጋፊ አካላት በመሆን ይገኛሉ።
ፋይኮሎጂስቶች በአብዛኛው የሚያተኩሩት በለጋውሃ ወይም በውቅያኖስ ዋቅላሚዎች ላይ ሲሆን፣ በተጨማሪ ከእነዚህ ዘርፎች ውስጥ ደግሞ በባልጩት ዋቅላሚዎች ወይም ለስላሳ አካል ባላቸው ዋቅላሚዎች ላይ ሊሰሩ ይችላሉ።
የፋይኮሎጂ ታሪክ
ለማስተካከልየጥንት ግሪኮችም ሆኑ ሮማውያን ስለ ዋቅላሚዎች ያውቁ ነበር፣ እንደውም የጥንት ቻይናውያን[1] አንዳንድ ዝርያዎችን እንደ ምግብ አድርገው ሲያመርቱ የነበር ቢሆንም፣ የዋቅላሚዎች ሳይንሳዊ ጥናት የተጀመረው በ18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መገባደጃ በ1757 በፔር ኦስቤክ አማካኝነት ፉከስ ማክሲመስ (አሁን ኤክሎኒያ ማክሲማ) ለተባለው ዝርያ ገለጻ እና ስያሜ በመስጠት ነበር።ይህን ተከትሎ እንደ ዳውሰን ተርነር እና ካርል አዶልፍ አጋርድ ባሉ ምሁራን የተሰራ ገላጭ ስራ ነበር፤ነገር ግን በዋቅላሚዎች ውስጥ ጉልህ ቡድኖችን የመፍጠር ሙከራዎች የተደረጉት በ19 ኛው ክፍለ ዘመን ማገባደጃ በጄቪ ላሞሮክስ እና በዊልያመ ሄንሪ ሃርቪ ነበር፡፡ ሃርቪ ዋቅላሚዎችን በቀለማቸው ላይ በመመስረት ወደ አራት ዋና ክፍሎች ስለመደበ በከፊል"የዘመናዊው ፋይኮሎጂ አባት" ተብሎ ተጠርቷል፡፡[2]
በ19 ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ እና በ 20 ኛው ክፍለ ዘመን መግቢያ ላይ ነበር ፋይኮሎጂ የራሱ ችሎ እውቅና ያለው መስክ የሆነው። እንደ ፍሬድሪክ ትራውጎት ኩትዚንግ ያሉ ሰዎች ገላጭ ስራውን ቀጥለው ነበር። በጃፓን ከ 1889 ጀምሮ ኪንታሮ ኦካሙራ ስለ ጃፓን የባህር ዳርቻ ዋቅላሚዎች ዝርዝር መግለጫዎችን ብቻ ሳይሆን ስለ ስርጭታቸውም አውዳዊ ትንታኔ ሰጥቷል።[3]
ምንም እንኳን አርኬ ግሬቪል አልጌ ብሪታኒኬን በ1830 ያሳተመ ቢሆንም፣ የመለያ ቁልፎች ዝግጅት፣ ሲስተማቲክ ኮሪሌሽን እና ሰፊ የስርጭት ካርታ ስራ የብሪታንያ የባህር ውስጥ ዋቅላሚዎች ካታሎግ በ1902 በአርነስተ ውስጥ በኤድዋርድ አርተር ሊዮኔል ባተርስ እስከታተመበት ጊዜ ድረስ አልነበረም።[4]
ከ1899-1900, አና ዌበር-ቫን ቦሴ የደች ፋይኮሎጂ ባለሙያ የሲቦጋ ጉዞን ከተጉዋዘች በኋላ በ 1904 “ዘ ኮራሊናሲዬ ኦፍ ዘ ሲቦንጋ ኤክስፔዲሽን” የተሰኘውን ህትመት አሳትማለች።[5]
እ.ኤ.አ. በ 1803 ዣን ፒየር ቫውቸር በዋቅላሚዎች ውስጥ ስላለው አይሶጋሚ(ጾታዊ ግንኙነት) ያሳተመው ህትመት ነበር፤ነገር ግን የዋቅላሚዎች ስርአተ እርባታ እና እድገት በስፋት መጠናት የተጀመረ በ20ኛው ክፍለዘመን መግቢያ ላይ ነበር። ፊሊክስ ዩዢን ፍሪሽ እ.ኤ.አ. በ1935 እና 1945 ያሳተማቸው የተደራጁ እትሞች ስለዋቅላሚዎች ስነቅርጽ እና ስር አተ እርባታ የታወቁ ነገሮች ተጠናቅረውባቸዋል።ይህን ተከትሎ በ1950ዎቹ በሜሪ ፓርኬ የሚመራ የአካባቢ ማረጋገጫ ዝርዝሮች ዝግጅት በ1931ዱ "ከማንክስ አልጌ" እትሟ ላይ፤እሱን ተከትሎ ደግሞ በ1953 "የብሪታንያ የባህር ዋቅላሚዎች የመጀመሪያ ደረጃ ማረጋገጫ ዝርዝር” በተሰኘው እትሟ ተሰርቷል። [6]
ምንም እንኳን የሊሊ ኒውተን የ1931 መመሪያ መጽሃፍ [7] ለብሪታንያ ደሴቶች ዋቅላሚዎች የመጀመሪያውን የመለያ ቁልፍ ያቀረበ ቢሆንም የእንደዚህ ዓይነቶቹ ቁልፎች መደበኛ የሆኑት ገና በ1960 ዎቹ ነበር።በ1980ዎቹ በስነ ምህዳር ላይ በአዲስ መልኩ ትኩረት መደረጉ[8] በዋቅላሚዎች ስብስብ ላይ እና በትላልቅ እጽዋት ስብስብ ውስጥ ዋቅላሚዎች ስላላቸው ስፍራ ተጨማሪ ጥናት ተደርጓል፤ እናም አካባቢአዊ ልዩነቶችን ለማስረዳት ተጨማሪ መሳሪያ አቅርቧል።.
እጅግ የበለጸገ የባህር አረም ያላት አህጉር አውስትራሊያ ስትሆን ወደ 2,000 የሚሆኑ ዝርያዎች ያሏት። [11]
ታዋቂ ፋይሎጂስቶች
ለማስተካከል- ኢዛቤላ አቦት(1919–2010)
- ካርል አዶልፍ አጋርድ(1785-1859)
- ጃኮብ ጆርጅ አጋርድ(1813-1901)
- ኤም ኤስ ባላክሪሽናን(1917-1990)
- ኤልሲ ኤም በሮውስ(1913–1986)
- ማርጋሬት ኮንስታንስ ሄለን ብላክለር(1902-1981)
- ኤልሲ ኮንዌይ1902-1992)፣ የብሪቲሽ ፋይኮሎጂካል ሶሳይቲ ፕሬዝዳንት1965-1967።
- ኢ. ዬል ድውሰን(1918-1966)
- ጆቫኒ ባቲስታ ዴ ቶኒ(1864-1924)
- ካትሊን ማርያም ድሩ-ቤከር(1901-1957)
- ሲልቪያ አሊስ ኤርሌ(1935-)
- ናትናኤል ሊዮን ጋርድነር(1864-1937)
- ሮበርት ኬይ ግሬቪል(1794-1866)
- ሚካኤል ዲ ጊሪ(1949-)
- ሊና ትሬሲ ሀንክስ(1879–1944)
- ኤም. ኦ. ፒ ላየንጋር(1886-1986)
- ኢፊዮን ጆንስ (1925-2004)
- ቫሱዴቫ ክሪሽናሙርቲ(1921-2014)
- ፍሬድሪክ ትራውጎት ኩትዚንግ(1807-1893)
- ማሪ ሊሞይን(1887-1984)
- ዳያን ኤስ.ሊለር(1945-)
- ሃንስ ክርስቲያን ሊንግቢ(1782-1837)
- ካሮላ ኢቬና ሚክል(1900-1970)
- አይሪን ማንቶን(1904-1988)
- ቫለሪ ሜይ(1916-2007)
- ካርል ንጌሊ(1817-1891)
- ሊሊ ኒውተን(1893-1981)
- ፍሬድሪክ ኦልትማንስ(1860-1945)
- ዊሊያም ጄ ኦስዋልድ(1919-2005)
- ሜሪ ፓርክ(1908-1989)
- ፍራንዝ ጆሴፍ(1814-1870)
- ዊልያም አልበርት ሴቼል(1864-1943)
- ፖል ሲልቫ (1922-2014)
- ጊልበርት ሞርጋን ስሚዝ(1885-1959)
- ጆን ስታክሃውስ (የእጽዋት ተመራማሪ) (1742-1819)
- ዊልያም ራንዶልፍ ቴይለር(1895-1990)
- ቪቶር ቤኔዴቶ አንቶኒዮ ትሬቪሳን ደ ሴንት-ሊዮን።(1818-1897)
- ጋቪኖ ትሮኖ ፣ (1931-) ፊሊፒናዊ የባህር ውስጥ ባዮሎጂስት በባህር ውስጥ አረም ላይ ምርምር ለማድረግ ተጠቅሷል።
- ማሪን ዴ ቫሌራ(1912-1984)
- አና ዌበር-ቫን ቦሴ(1852-1942)
- ጆርጅ ስተፈን ዌስት (1876-1919)
- ዊልያም ዌስት (የእጽዋት ተመራማሪ) (1848-1914)
- ዊልያም ዌስት ጁኒየር(1875-1901)
- ካርል ሉድቪግ ዊልደንኖቭ (1765-1812)
ዋቢ ምንጮች
ለማስተካከል- ^ Porterfield, William M. (1922) "References to the algae in the Chinese classics" Bulletin of the Torrey Botanical Club 49: pp. 297–300
- ^ "About Phycology" Lance Armstrong Foundation
- ^ Tokida, Jun and Hirose, Hiroyuki (1975) Advance of Phycology in Japan Junk, The Hague, Netherlands, page 241, ISBN 90-6193-026-X
- ^ Batters, Edward Arthur Lionel (1902) A catalogue of the British Marine Algae being a list of all the species of seaweeds known to occur on the shores of the British Islands, with the localities where they are found Newman, London, OCLC 600805992, published as a supplement to Journal of Botany, British and Foreign
- ^ Weber-Van Bosse, A.; Foslie, M. (1904). The Corallinaceae of the Siboga-expedition. F. J. Brill.
- ^ Parke, Mary W. (1953) "A preliminary check-list of British marine algae" Archived ኦገስት 26, 2011 at the Wayback Machine መለጠፊያ:Webarchive Journal of the Marine Biological Association of the United Kingdom 32(2): pp. 497–520; revised and corrected through the third revision of 1976
- ^ Newton, Lily (1931) A Handbook of the British Seaweeds British Museum, London
- ^ Walter, Heinrich and Breckle, Siegmar-Walter (1983) Ökologie der Erde: : Geo-Biosphäre: Band 1, Ökologische Grundlagen in globaler Sicht (Ecology of the Earth: the geobiosphere: Volume 1, Ecological principles in a global perspective) Fischer, Stuttgart, Germany, ISBN 3-437-20297-9; in German
- ^ Stevenson, R. Jan; Bothwell, Max L. and Lowe, Rex L. (1996) Algal ecology: freshwater benthic ecosystems Academic Press, San Diego, California, page 23, ISBN 0-12-668450-2
- ^ Figueiras, F. G.; Picher, G. C. and Estrada, M. (2008) "Chapter 10: Harmful Algal Bloom Dynamics in Relation to Physical Processes" page 130 In Granéli, E. and Turner, J. T. (2008) Ecology of Harmful Algae Springer, Berlin, pp. 127–138, ISBN 3-540-74009-0
- ^ "Marine algae". Royal Botanic Gardens & Domain Trust. Archived from the original on 2015-09-06. በ2023-11-03 የተወሰደ.