ፉንግ ወይንም ዳር ፉንግ በምስራቅ ሱዳን የሚገኝ ብሔረሰብ ነው። የህብረተሰቡ አነሳስ ጠርቶ ባይታዎቅም ነገር ግን በ15ኛው ክፍለ ዘመን ማብቂያ ከደቡብ ሱዳን ወደ ኑቢያ ፈልሰው እንደመጡ ግንዛቤ አለ።

ከነሱ ወደ አካባቢው መምጣት በፊት፣ አብደላህ ጃማ የተባለ መሪ በአሁኑ ምስራቅ ሱዳን ፣ የተሰባጠሩ ግዛቶችን አቋቁሞ ነበር። ይሁንና ፉንጎች ከደቡብ ወደዚህ ክፍል በፈለሱ ጊዜ፣ እነዚህ የተበታተኑ ግዛቶችን አንድ በማድረግ የስናር ግዛትን አቋቋሙ። ይሄ የሆነው በመሪያቸው አማራ ደንቃስ በ1496 ዓ.ም. ነበር።

የስናር ግዛት ለ300 ዓመታት እየተጠናከረ እና እያደገ ሂዶ፣ ኋላ ላይ በውስጡ በተነሳ ቅራኔ ተዳክሞ ሲንገዳገድ፣ የግብጽ ገዢ የነበረው መሃመድ አሊ ፓሻ በ1813 ዓ.ም. ሲያጠቃው ሙሉ በሙሉ አበቃለት።

ፉንጎች አሁን የአረብኛ ተናጋሪ ሲሆኑ፣ ከ1948ዓ.ም. በኋላ የአሁኑ ሱዳን አካል ሁነው ዋና ከተማቸው ስናር ይባላል።


ደግሞ ይዩ፦