ፀሐይ ዮሐንስ (፲፱፻፶፬ ዓ.ም. ተወለደ[1][2]) የኢትዮጵያ ታዋቂ ዘፋኝ ሲሆን ብዙ ዘመናዊ የሙዚቃ ስራወችን በማቅረብ ይታወቃል።

ፀሓየ ዮሓንስ

የሕይወት ታሪክ ለማስተካከል

ፀሐይ ዮሐንስ በ፲፱፻፶፬ ዓ.ም. በኤርትራ ክፍለ ሀገር አሥመራ ከተማ ተወለደ። ፀሐይ ከአባቱ ጋር ወደ አዲስ አበባ መጥቶ ትምህርቱን በሚከታተልበት ወቅት የሙዚቃ ችሎታውን ለማዳበር ቻለ። የ፭ኛ ክፍል ተማሪ እያለ በአብዮቱ ወቅት ፷ ሺህ ተማሪዎች ወደ ገጠሪቱ ኢትዮጵያ ለዕድገት በሕብረት ዘምተው ሳለ «በርታ ዘመዴ ዘማቹ ጓዴ» የተሰኘው የመጀመሪያውን ሙዚቃ ለሕዝብ በማቅረብ በወቅቱ ከፍተኛ አድናቆት ተችሮታል።[1]

ከዚያም መሀይምነትን ለማጥፋት የመሠረተ ትምህርት ዘመቻ በታወጀበት ጊዜ «ማንበብና መፃፍ» የተሰኘው ዘፈኑ በጣም ቀሽቃሽና አስተማሪ ስለነበር ፀሐይን ይበልጥ እንዲታወቅ አድርጎታል።[1]

ከእነዚህም ማህበራዊ ሕይወትን ከሚገልፁት በተጨማሪ በ፲፱፻፸፭ ዓ.ም. ካሰማቸው ዘፈኖቹ ውስጥ «ፍንጭትዋ»፣ «ያዝ ያዝ» እና «ጡር ነው» የተሰኙት በሕዝቡ ዘንድ ውዴታን ያገኙ ነበሩ። ፀሐይ አሁንም ቢሆን የተለያዩ ዜማዎችን በመዝፈን በሕዝቡ ዘንድ ከፍተኛ አድናቆት ያለው አርቲስት ነው። [1]

የሥራዎች Archived ኦገስት 9, 2020 at the Wayback Machine ዝርዝር ለማስተካከል

ማጣቀሻዎች ለማስተካከል

  1. ^ "ናሽናል ቢብሊዮግራፊ ቡድን፣ የአንጋፋ አርቲስቶች መዝገበ የሕይወት ታሪክ፣ መጋቢት ፳፻፣ ገጽ 22". Archived from the original on 2011-09-29. በ2010-12-05 የተወሰደ.
  2. ^ (እንግሊዝኛ) የፀሐይ ዮሐንስ ድረገጽ (በኅዳር ፳፮ ቀን ፳፻፫ ዓ.ም. የታየ) Archived ሴፕቴምበር 19, 2008 at the Wayback Machine