ግብጽኛ (ግብጽኛ፦ እርኒታዊ) ቀድሞ በጥንታዊ ግብጽ የተነገረው ቋንቋ ነበር። በአፍሮ-እስያዊ ቋንቋዎች ውስጥ ይመደባል። ይህ ማለት ለሴማዊ ቋንቋዎች ሩቅ ዝምድና አለው።

የቋንቋው ኗሪ ስም «እርኒታዊ» ትርጉም «የኹለት አገር አፍ» ሲሆን፣ ቃል በቃል /እር/ «አፍ»፣ /ኒ/ «የ»፣ /ታ/ «አገር»፣ /ዊ/ «ኹለት» ነው።

የተጻፈው «የግብጽ ሃይሮግሊፊክስ» በተባለ የስዕል ጽሕፈት ነበረ። መጀመርያ የታወቁት ሃይሮግሊፎች ከ3125 ዓክልበ. ገደማ ሲሆኑ መጨረሻውም በ386 ዓም ተቀረጸ። ከዚያን ጊዜ በኋላ የሃይሮግሊፍ ዕውቀት ቢጠፋም፣ የግብጽኛ ተወላጅ የሆነው ቅብጥኛ በግብጽ ክርስቲያኖች ዘንድ ከግሪክ አልፋቤት በደረሰው ቅብጢ አልፋቤት ሲጻፍ ቀርቷል። የጥንቱ ሃይሮግሊፍ ማንበብ ችሎታ የተፈታው በ1814 ዓም የሮዜታ ድንጊያ ከተገኘ በኋላ ነበር።

የግብጽኛ ጸባይ ከነዚሁ ቋንቋዎች ወላጅ ከ«ቅድመ-አፍሮ-እስያዊ» ብዙ እንደ ረሳ ይመስላል።

ከሌላው ጥንታዊ ልሳን ከግዕዝ ጋራ ሲነፃፀር ዝምድናው በጥቂት ቃላት እንዴት እንደ ወረደ ይታያል፦

ግዕዝ ግብጽኛ ትርጉም
ነፍኀ ነፊ ነፋ
ጼነው ሰን አሸተተ
ተንፈሰ ተፐር ተናፈሰ
ቀዓ ቀዓእ አስታወከ
ነሰከ ፐዘኽ ነከሰ
ነአወ ኑ (ነወ) አደነ
አእምረ ረሕ አወቀ
ሰሐበ ሰጭአ ሳበ
ሰምአ ሰጀም ሰማ
ቀተለ ኸደብ ገደለ
አረጋዊ ኢአዊ አሮጌ
የመን ኢመን ቀኝ
ጸጋም ሰምሒ ግራ
ንዑስ ነጀስ ትንሽ
ልብ ኢብ ልብ
ልሳን ነስ ምላስ
ሽዕርት ሸኒ ጽጉር
አማዑት መሕቱ ሆድቃ
ዖፍ አፐድ ወፍ
ወልድ ኸረድ ልጅ
ማይ ሙ (መወ) ውሃ
ጊሜ ሲም ጉም
ኮከብ ሰብአ ኮከብ
ምሉእ መሕ ሙሉ

እነዚህ ቃሎች ከሷዴሽ ዝርዝሩ 1/8 ያህል ሩቅ ተመሳሳይነት ያሳያሉ። በተረፉት 7/8 ያህል ባጠቃላይ ብዙ ተመሳሳይነት አልተጠበቀም።

ደሞ ይዩ፦

ለማስተካከል