ጊዜዋ ወይም ግጃዋ (Withania somnifera) እስያኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ቊጥቋጥ ተክል ነው። የአውጥ አስተኔ አባል ነው።

ግጃዋ

የተክሉ ሳይንሳዊ ጸባይ ለማስተካከል

ብዙ ከረም አጭር ቊጥቋጦ ነው። ትንንሽ አረንጓዴ አበቦች አሉት። የበሰለው ፍሬ ከብርቱካን እስከ ቀይ ቀለም ድረስ ይለውጣል።

አስተዳደግ ለማስተካከል

አንዳንድ ፈንገስ ወይም ተኋን አይነቶች ይበሉታል።

በብዛት የሚገኝበት መልክዓ ምድር ለማስተካከል

አሿጋንዳ በተለይ በሕንድ በብዙ ደረቅ ክፍላገሮች፣ በኔፓልቻይና እና የመን ውስጥ ይታደጋል።

የተክሉ ጥቅም ለማስተካከል

ትንሹ እንጆሪ ፍሬ በሕንድ አንዳንዴ አይብን በመሥራት ይጠቀማል። እንዲሁም በኢትዮጵያ ጠላ በመሥራት እንደ ጠቀመ ተብሏል (አቢሲኒካ)።

ተክሉ በሕንድ አገር አሿጋንዳ ተብሎ ረጃጅም ሥሮቹ በሕንድ ባሕላዊ ሕክምና (አዩርቬዳ) ከጥንት ጀምሮ ተጠቅመዋል። ብዙ መድሃኒት ፈውሶችና እድሜ የሚጨምር እጽ መሆኑ በሰፊው ቢታስብም ይሄ በዘመናዊ ሊቃውንት ገና አልተረጋገጠም።

በየመን አገር ተክሉ ኡባብ ተብሎ የደረቅ ቅጠሉ ዱቄት ልጥፍ ለቁስልና ለመቃጠል ይለጠፋል።