ዳንዡ
ዳንዡ (ቻይንኛ፦ 丹朱) የጥንታዊ ቻይና (ኋሥያ) ንጉሥ ያው ልጅ ነበረ። እናቱ የያው ቁባት ሳን ዪ ተባለች።
ንጉሥ ያው ልጁን ዳንዡ ለማስደሰት «ወይጪ» (ወይም «ጎ») የተባለውን ጨዋታ የፈጠረው ነበር። ዳንዡ ግን እንደ አባቱ ምግባረ ጥሩ ሳይሆን ግፈኛና ባለጌ ስለሆነ አባቱ ወደ ዳንሽዌ አባረረው ይባላል።[1]
የቀርከሃ ዜና መዋዕል በተባለው ጽሑፍ ዘንድ፣ ያው በ58ኛው ዘመነ መንግሥት (2076 ዓክልበ.) ዳንዡን አባረረው፣ ከዚያም ሚኒስትሩን ሹንን እንደ ተከታይ ሰየመው፤ በ73ኛውም አመት (2061 ዓክልበ.) ያው የኋሥያን ዙፋን ትቶ ለተከታዩ ለሹን ሰጠው። ሹን ንጉሥ እየሆነ ዳንዡ ከሹን ይራቅ ነበር። በ2033 ዓክልበ. ያው ባረፈበት ጊዜ ሹን ዙፋኑን ለዳንዡ ለመስጠት ፈቃደኛ ቢሆንም፥ «ይህ ግን በከንቱ ነበረ»።
በአንዱ መዝገብ እንደሚገለጽ፣ «የችሎት ክስ ጉዳይ ያለው ሁሉ ወደ ሹን እንጂ ወደ ዳንዡ አይሄድም ነበር»።[2]
ዳንዡን ንጉሥ ማድረጉ ስላልተቻለ፣ በዘውዱ ፈንታ ታንግ በተባለ ክፍላገር ውስጥ አንድ ትንሽ ግዛት ተሰጠው።[3]
በሌላ ቦታ ግን የቀርቀሃ ዜና መዋዕል በፍጹም ሌላ አስተያየት ይሰጣል። በዚህ መሠረት ሹን ያውን ከዙፋኑ ገልብጦ በእስር ቤት አኖረው፣ በፈንታውም ዳንዡን ለአጭር ጊዜ ንጉሥ አደረገው፣ ከትንሽ በኋላ ግን ሹን ዙፋኑን ለራሱ ያዘው።
ዋቢ ምንጮች
ለማስተካከል- ^ Yang, Lihui; Deming An, Jessica Anderson Turner (2005). Handbook of Chinese mythology. ABC-CLIO Ltd. p. 228. ISBN 978-1-57607-806-8. http://books.google.co.uk/books?id=Wf40ofEMGzIC&pg=PA228&dq=Yao+is+said+to+have+invented+the+game+of+Weiqi&hl=en&ei=lAfVTIruBdO3hAfCuIjVBA&sa=X&oi=book_result&ct=result&resnum=3&sqi=2&ved=0CDIQ6AEwAg#v=onepage&q&f=false. (እንግሊዝኛ)
- ^ Heiner Roetz (1993). Confucian ethics of the axial age: a reconstruction under the aspect of the breakthrough toward postconventional thinking. SUNY Press. p. 37. ISBN 0-7914-1649-6. http://books.google.com/books?id=zNbsbDlIRkUC&pg=PA37#v=onepage&q=shun%20succeeded%20yao%20danzhu%20lawsuit%20procedure&f=false በ4-1-2012 የተቃኘ. (እንግሊዝኛ)
- ^ J. Michael Farmer (2007). The talent of Shu: Qiao Zhou and the intellectual world of early medieval Sichuan (illustrated ed.). SUNY Press. p. 203. ISBN 0-7914-7163-2. http://books.google.com/books?id=ZeErCtp5_cUC&pg=PA203#v=onepage&q&f=false በ4-1-2012 የተቃኘ. (እንግሊዝኛ)