ደር
ደር የሱመር ጥንታዊ ከተማ ነበር። ዛሬው ሥፍራው ተል አካር ተብሎ በዘመናዊው አገር ኢራቅ ውስጥ ይገኛል። እስካሁን ድረስ ይህ ቦታ በሥነ ቅርስ መርማሪዎች አልተቆፈረም።
ደር (ተል አካር) | |
---|---|
ሥፍራ | |
መንግሥት | አካድ፣ ዑር፣ ላርሳ፣ ባቢሎኒያ፣ አሦር፣ ኤላም ወዘተ. |
ዘመን | 2075-630 ዓክልበ. ግድም |
ዘመናዊ አገር | ኢራቅ |
ጥንታዊ አገር | ሱመር |
ታላቁ ሳርጎን ከተማውን ለአካድ መንግሥት ያዘ፤ ተከታዩም ሪሙሽ ከንቲባውን ማረከና ከተማውን አጠፋ። በዑር መንግሥት ዘመን በ1945 ዓክልበ. ሹልጊ ደግሞ ደርን አጠፋ። ለትንሽ ጊዜ ደር የኤሙትባል ነጻ መንግስት መቀመጫ ሆነ፣ ንጉሡም ኤሽኑናን በቢላላማ ዘመን ዘረፈው።
እንዲሁም የላርሳ ንጉሥ በ1715 ዓክልበ.፣ የባቢሎን ንጉሥ አሙ-ዲታና በ1559 ዓክልበ. ደርን አጠፉ። ከዚህ በኋላ ደር የኤላምን ጠረፍ የሚወስን አምባ ይባላል። በ1118 ዓክልበ. ግድም የባቢሎን ንጉሥ 1 ናቡነደነጾር ኤላምን ከደር አንሥቶ ወረረ። በ1050 ዓክልበ. በተከታዩ አዳድ-አፕላ-ኢዲና ጊዜ አራማውያን ባቢሎኒያን ከሶርያ ወርረው ደርን አጠፉ። በ900 ዓክልበ. ግድም የአሦር ንጉሥ 2 አዳድ-ኒራሪ ደርን ከባቢሎኒያ ግዛት ያዘው። በ821 ዓክልበ. ደግሞ የአሦር ንጉሥ 5 ሻምሺ-አዳድ የባቢሎንን ንጉሥ ማርዱክ-ባላሡ-ኢቅቢን በደር ማረከው።
በ728 ዓክልበ. በደር በአንድ ታላቅ ውግያ የባቢሎን ንጉሥ 2 ማርዱክ-አፕላ-ኢዲና እና የኤላም ንጉሥ 1 ሁምባኒጋሽ አንድላይ የአሦርን ንጉሥ 2 ሳርጎንን አሸነፉት። በ631 ዓክልበ. ደር በአመጽ ከአሦር መንግሥት ተለየ።