ደረስጌ ማርያም
(ከደራስጌ ማርያም የተዛወረ)
ደረስጌ ማርያም ደባርቅ፣ ጎንደር ውስጥ ደረስጌ (ደብረ-ስጌ ከሚለው ስም የመጣ)፣እሚባል ቦታ የሚገኝ ቤተ ክርስቲያን ነው። በዘመነ መሳፍንት ገነው የነበሩት ደጃች ውቤ እራሳቸውን ለማንገሥ ሲሉ የጀርመኑን ሠዓሊ እና ሳይንቲስት ዶክተር ሺምፐር በመቅጠር በ1840ዎቹ መጀመሪያ ያስገነቡት ቤተክርስቲያን ነው። በኋላ ላይ ከወደፊት ዓፄ ቴዎድሮስ ጋር በዚሁ አካባቢ ጦርነት ገጥመው ስለተሸነፉ ፣ ራስ ውቤ ለስርዓተ ንግሣቸው ባሠሩት ቤተ ክርስቲያን ዓፄ ቴዎድሮስ በአቡነ ሰላማ እጅ ተቀብተው ዘውድ ጭነው ነገሡበት። ይሄውም በ1847 መሆኑ ነው።
-
አጼ ቴዎድሮስ ንግስናቸውን ያወጁበት ሰገነት፣ስሜን ጃናሞራ፣ደረስጌ ማርያም
ደረስጌ ማርያም | |
ደረስጌ ማርያም | |
ከፍታ | 3035 ሜትር |