የጄኖቫ ቅዱስ መልክጄኖቫጣልያን በተገኘው ቅዱስ በርተሎሜዎስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚገኝ ስዕል ነው። ይህ ስዕል የኢየሱስ ክርስቶስ መልክ ለመግለጽ እንደታሠበ ይታመናል።

በጄኖቫ የሚገኘው 'ቅዱስ መልክ'

በአንድ ትውፊት ዘንድ፣ ኢየሱስ በሕይወቱ ስብከት ሳለ የኦስሮኤኔ (በሶርያ) ንጉሥ 5 አብጋር በበሽታ ታምመው ኢየሱስ መጥቶ እንዲፈውሳቸው አንድን መልእክተኛ (ሐናን) ወደ ኢየሩሳሌም ልከው ነበር። ኢየሱስ ወደ ከተማው ወደ ኤደሣ ለመሔድ ጊዜ ስላልነበረው፣ ባንድ ጨርቅ ላይ መልኩን በተአምር አሳተመና ሐናን ስዕሉን ይዞ ወደ ንጉሡ እንዲሔድ ላከው። እንዲህም ሆኖ አብጋር ይህን ስዕል አይተው ከበሽታቸው ተፈወሱና ወዲያው ምዕመን ሆኑ። ስዕሉ ደግሞ በተአምር በመፈጠሩ 'ያለ እጅ የተሠራው' ተብሏል።

በጥንታዊ ታሪክ መጻሕፍት መሠረት ይህ ታምራዊ መልክ ያለበት ስዕል እስከ 936 ዓ.ም. በኤደሣ ቆይቶ በዚያ አመት ወደ ቢዛንታይን ዋና ከተማ ወደ ቊስጥንጥንያ ተዛወረ። እዚህም ፈረንጆች (መስቀለኞች) ከተማውን እስከ ዘረፉት አመት እስከ 1196 ድረስ እንዳደረ ይባላል። ከዚያ በኋላ ምን እንደሆነበት ባይታወቀም ብዙ ቅጂዎች ስለተደረጉበት በአውሮጳ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ አንዳንድ ቅጂ ዕውነተኛው መልኩ እንዳሉ የሚል ልማድ አለ።

በቫቲካን ከተማ ያለው ቅጂ

እንግዲህ በጄኖቫ ብቻ ሳይሆን በቫቲካን ከተማ ሮማ ተመሳሳይ ስዕል ቢገኝ እሱ እውነተኛው መሆኑ የሚያምኑ አሉ።

በጄኖቫ ያለው ስዕል መገኛ የጄኖቫ ዶጄ (መስፍን) ሌዮናርዶ ሞንታልዶ1376 ዓ.ም. ለበርተሎሜዎስ ቤተክርስቲያን እንዳወረሰው ይባላል። በተጨማሪ ሞንታልዶ ያገኘው፣ የቢዛንታይን ንጉሥ 5 ዮሐንስቱርኮች በወረሩበት ዘመን እርዳታ ስለ ሰጠ፣ ዮሐንስ ስዕሉን ስለ ወሮታው በምላሽ እንደ ሠጡት ይታመናል።

የጣልያዊት ሊቅ ኮለት ዱፎር ቦዞ1961 ዓ.ም. ብዙ ልዩ ትንትና አድርጋ፣ የጄኖቫ ስዕል በሳንቃ ላይ የተለጠፈ ጨርቅ ከወርቃም ከፈፍ በታች መሆኑን ገለጠች።

ደግሞ ይዩ፦ የቶሪኖ ከፈን

ዋቢ መጽሕፍት

ለማስተካከል

ዋቢ ድረገጽ

ለማስተካከል