ስዕል ማለት በስሌዳ ላይ በቀለምም ይሁን በጠመኔ አለዚያም በርሳስና በሌላ ነገር ተስርቶ በዓይን በማየት የሚገነዘቡት ጥበብ ነው። ለዓይንና ለመንፈስ ከሚስጠው አርካታ ሌላ ፡ ያንድን ህብረተስብ ብሎም የኪነ ጥበቡን ስው ዓመለካከት ይጠቁማል ተብሎ ስለሚታመን በዘመናዊ ዓለም የተለየ እንክብካቤ የተስጠው የስው ልጅ ጥበባዊ ተግባር ነው። የዚህ አይነት ጥበብ የሚስራው ደገሞ ስዓሊ ይባላል።

አዲስ አበባ ሥነ ጥበብ ት/በት የመጀመሪያው ርዕስ መምህር የነበረው አለ ፈለገ ስላም ስለ ስዕል ትምህርት ስያብራራ: «የስዕል ትምህርት የስውን -የእንስሳን -ያገርን -የደመናን - በጠቅላላው የሥነ ፍጥረትን መልክና ባሕርይ አጥኝ ሁኖ የራሱን ስሜት በግሉ እየፈጠረ በቀለምና በልዩ ልዩ መሳሪያዎች ከጠፍጣፋ ነገር ላይ ስርቶ ማውጣትን፥ በሐውልት ትምህርት ደግሞ አንደ ስዕሉ የተዘረዘረውን ሓሳብ ከጠፍጣፋ ነገር ላይ በመስራት ፈንታ ጠንካራ ከሆነ አካል ላይ በድንጋይ፥ በአንጨት፥ በዝሆን ጥርስ ወይም በነሐስ ቅርጽና መልክ ጻልቶ ማውጣት ነው።» በማለት ግለጸ።

ስመጥር ገብረ ክርስቶስ ደስታ ደግሞ ፡ «በዘመናዊ አቅድ ስዕል ራሱ ሐሳብ ነው። የኣንድ ነገር ሁኔታ የአንድ ነገር ትርጉምና ስሜት ነው...። ዛሪ ስው ራሱን ብቻ መመልከት ትቶ ዓለም ከብዙ ርቀት ከብዙ በኩል ሲታይ ምን ኣይነት ስሜት አንደሚስጥ - አለማዊ ዘላለማዊ የሆነውን ነገር በመተርጎም - በዓይን የሚታይ፥ የቀለም፥ የመስመርና የቅርጽ ሙዚቃ ለመፍጠር ይጥራል።» በማለት ተናግሯል።

  • ደብረ ሐይቅን ተመልከት -

http://www.ethiopianart.org