የኖቪባዛር ሳንጃክ
የኖቪ ባዛር ሳንጃክ (ሰርብኛ፦ Novopazarski sandžak/Новопазарски санџак; ቱርክና፦ Yeni Pazar sancağı) ከ1856 እስከ 1905 ዓም. ድረስ የኦቶማን መንግሥት ሳንጃክ ወይም አስተዳደር ክልል ነበረ። በዛሬው ሞንቴኔግሮ፣ ሰርቢያ እና ኮሶቮ ውስጥ የተገኘው ሲሆን[a]አሁን «ራሽካ» እና «ሳንጃክ» ይባላል።
በኦቶማን ቱርክኛ «ሳንጃክ» ማለት አስተዳደር ክልል ከመሆን በላይ፣ «ሰንደቅ» ደግሞ ማለት ነው፣ እንዲሁም የአማርኛ ቃል «ሰንደቅ» መንስኤ ነው።
ታሪክ
ለማስተካከልየኦቶማን ግዛት
ለማስተካከልበ1447 ዓም አካባቢ የኦቶማን ቦስኒያ አለቃ ኢሳ-በግ ኢሳኮቪች ከሰርቢያ ደስፖታት መንግሥት ደቡብ-ምዕራብ ክፍሎች በያዘ ጊዘ፣ የኖቪ ባዛር መንደር ገና አልኖረም ነበር፤ በዙሪያው የተገኙት መንደሮች ፖቶክና ፓሪጸ ብቻ ነበሩ። በ1448 ዓም ኢሳኮቪች መንደሩን መሠረተ፤ ገበያ ወይም በቱርክኛ «ፓዛር»፣ መስጊድ፣ የሕዝብ መታጠቢያ ቤት፣ ሆስተልና ግቢ ሠራበት።[1] በመጀመርያ ኖቪ ፓዛር መንደር በጀለጽ ቪላየት (ክፍላገር) በስኮፕየ ጠረፍ አውራጃ ተገኘ።[2] በ1455 ዓም ጀለጽ ወደ ቦስኒያ ሳንጃክ ተጨመረ። ከዚያ በ1477 ዓም መቀመጫው ከጀለጽ ወደ ኖቪ ፓዛር ተዛወረ።[3] ከዚህ የተነሣ የተለየ የኖቪ ፓዛር ሳንጃክ በሩሜሊያ ኤያሌት ውስጥ ተደረገ። በ1572 ዓም የቦስኒያ ሳንጃክ ወደ ኤያሌት ደረጃ በገባችበት ዘመን የኖቪ ፓዛር ሳንጃክ ወደ ቦስኒያ ኤያሌት ተመለሰ። በዚያም እስከ 1856 ዓም ይቆይ ነበር።
መሠረት
ለማስተካከልበ1856 ዓም የኦቶማን የቪላዬት ሕግ በወጣበት ጊዜ፣ የቦስኒያ ኤያሌት ተጨረሰና ኖቪ ፓዛር ብቸኛ ሳንጃክ ሆኖ መቀመጫው ኖቪ ፓዛር ከተማ ነበረ። በኋላ በ1870 ዓም ወደ አዲሱ ኮሶቮ ቪላዬት ተጨመረ። በኖረበት ዘመን ሁሉ፣ የዛሬው ሳንጃክ አውራጃ (ከኖቪ ባዛሩ ሳንጃክ ተሰይሞ) ወይም ራሽካ፣ ከዚህም በላይ የኮሶቮ ስሜን ክፍል ያጠቅልል ነበር።
የቤርሊን ጉባኤ (1870 ዓም)
ለማስተካከልበ1870 ዓም በተካሄደው ቤርሊን ጉባኤ፣ የኦስትሪያ-ሀንጋሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንድራሢ የቦስኒያና ሄርጸጎቪና ክፍላገር በኦስትሪያ ሠራዊት ከመያዝ በላይ፣ የአውስትሪያ ወታደሮች በኖቪባዛር ሳንጃክ ውስጥ እንዲቆዩ መብቱን አገኘላቸው። ነገር ግን እነዚህ ግዛቶች በስም የኦቶማን ክፍላገሮች ሆነው ቀሩ። በተጨማሪ፣ የኖቪባዛር ሳንጃክ ከሰርቢያና ሞንቴኔግሮ ግዛቶች መካከል በመቀመጡ እንደ ጠቀሜታ ተቆጠረ። እንዲሁም በዚያ ያሉት የኦስትሪያ ወታደሮች መንገድ ወደ ሳሎኒካ ለመክፈት እንደጠቀሙ በኦስትሪያ ባለሥልጣናት ዘንድ ይነገር ነበር።[4] [5]
የኦቶማን ክልል የነበረቸው ቦስኒያ በኦስትሪያ አስተዳደር መኖርዋ ይሁንና እስከ ሳሎኒካ ድረስ ለመዘመት የሚለው ሀሣብ በተቃራኒ ወገኖች በተለይም በሀንጋራውያን ዘንድ ተቃወመ። ነገር ግን ሰርብያና ሞንቴነግሮ እንዳይዋሕዱ እንዲሁም የሩስያ ተጽእኖ በባልካኖች ውስጥ እንዳይስፋፋ በመከልከሉ የኖቪባዛር መያዝ ጥቅም አይተው ታገሡት።
የኦቶማን አስተዳደር ለውጦች
ለማስተካከልየኦቶማን መንግሥት መሪዎች በራሳቸው በኩል በ1871 ዓም የኦስትሪያን ተጽእኖ ለመወሰን ኖቪባዛር ሳንጃኩን ከቦስኒያ ቪላዬት (መቀመጫ ሳራዬቮ) ለይተው ወደ ኮሶቮ ቪላዬት (መቀመጫ ፕርሽቲና) አዛውረው ጨመሩት።[6][7] በ1872 ዓም በይፋ ሳንጃኩን አካፍለው የኦስትሪያ ወታደሮች የበዙባቸው ሠፈሮች የፕልየቭሊያ ሳንጃክ ሆነው የተረፉት ሠፈሮች የስየኒጻ ሳንጃክ ተብለው ተደረጉ።[6]
የኦስትሪያ ወታደሮች በ1901 ዓም ሳንጃኩን መተዋቸው
ለማስተካከልበ1900 ዓም ኦስትሪያ ባቡር ወደ ኦቶማን መቄዶን ግዛት ለመሥራት የሚለውን ሀሣብ አሳወቀ። ይህ ባቡር በሳንጃኩ መካከል ይሄድ ነበርና በአውሮፓ አገራት መካከል ቀውስ ሆነ። እንዲሁም ቦስኒያ ወደ ኦስትሪያ-ሀንጋሪ ግዛት በይፋ ለመጨምር ያለው ሀሣብ በአገራት ዘንድ በጣም አከራካሪ ሆነ። ነገር ግን ቦስኒያ ወደ ኦስትሪያ መጨመሩ ዕውቅና ከሩስያ እንዲገኝ በምላሽ የኖቪባዛር ሳንጃክ ወደ ኦቶማን ቱርክ መንግሥት እንዲመለስ ተስማሙ።[8] እንግዲህ በዚያን ጊዜ የኦስትሪያ-ሀንጋሪ ወታደሮች ሳንጃኩን ተዉና ለ30 ዓመታት በኦስትሪያ አገዛዝ የነበረችው የቦስኒያ ቪላዬት በይፋ ወደ ኦስትሪያ ተጨመረች።
የ1905 ዓም. ባልካን ጦርነቶችና የኦቶማን አገዛዝ መጨረሻ
ለማስተካከልበመጀመርያው ባልካን ጦርነት 1905 ዓም የሞንተኔግሮና የሰርቢያ ሠራዊት ሳንጃኩን በቶሎ ያዙ። ከጦርነቱ በኋላ በሎንዶን ውል የሳንጃኩ መሬት በሰርቢያና በሞንቴነግሮ ተካፈለ።
ሕዝብ
ለማስተካከልየኖቪባዛር ሳንጃክ ሕዝቦች በተለይ ስላቭኛ የሚናገሩ እስላሞች፣ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን ሰርቦች፣ የአልባኒያዊ እስላሞችና ቱርኮች ነበሩ።
ከተሞች
ለማስተካከል
- ኖቪ ፓዛር
- ስየኒጻ
- ፕሪየፖልየ
- ኖቫ ቫሮሽ
- ፕሪቦይ
- ኮሶቭስካ ሚትሮቪጻ
- ፕሊየቭሊያ
- ቢየሎ ፖልየ
- በራነ
- ሮዣየ
a. | ^ Kosovo is the subject of a territorial dispute between the Republic of Kosovo and the Republic of Serbia. The Republic of Kosovo unilaterally declared independence on 17 February 2008, but Serbia continues to claim it as part of its own sovereign territory. The two governments began to normalise relations in 2013, as part of the Brussels Agreement. Kosovo has been recognised as an independent state by 108 out of 193 United Nations member states. |
- ^ Mihailo Maletić (1969). Novi Pazar i okolina. Književne novine. p. 107. https://books.google.com/books?id=mV48AAAAMAAJ በ24 January 2013 የተቃኘ. "Ако се (1455) помињу села Поток и Парице, а град не, то би значило да му још тада нису били ударени темељи. Изгледа ца се Иса-бег Исхаковић одлучио на изградњу града-утврђен>а већ 1456. године када имамо прве помене о Новом Пазару. Јиречек, наводећи које је све градове 1456. године заузео Мехмед II Освајач, каже: ,,Те, 1456."
- ^ Katić, Tatjana (2010), "Vilajet Pastric (Paštrik) 1452/1453 godine" (in Serbian), Micelleanea, Belgrade: Istorijski Institut, http://www.scribd.com/doc/86086432/50378999-Tatjana-Kati%C4%87-Vilajet-Pa%C5%A1trik-1452-53-godine
- ^ Hazim Šabanović (1959). Bosanski pašaluk: postanak i upravna podjela. Naučno društvo NR Bosne i Hercegovine. p. 118. https://books.google.com/books?id=kkQQAAAAIAAJ በ27 January 2013 የተቃኘ. "središta iz Jeleča u Novi Pazar izvršeno svakako nešto prije 1485 g., kada je Jeleč već bio izgubio raniji strateški značaj, a Novi Pazar, kome je Isa-beg Ishaković udario temelje još šezdesetih godina XV st. razvio se dotle u veću varoš."
- ^ Albertini, Luigi (1952). The Origins of the War of 1914. Volume I. Oxford University Press. p. 19.
- ^ Albertini, Luigi (1952). The Origins of the War of 1914. Volume I. Oxford University Press. p. 33.
- ^ ሀ ለ Milić F. Petrović (1995). Dokumenti o Raškoj oblasti: 1900-1912. Arhiv Srbije. p. 8. https://books.google.com/books?id=L1K5AAAAIAAJ. "Да би сузбила аустроугарски утицај у западним крајевима Рашке области, Турска је извршила нову управну поделу. Новопазарски санџак је 1879. год. издвојен из Босанског вилајста и прикључен Косовеком вилајету, који је основан још 1877. год. са седиштем у Приштини а касније у Скопљу. Потом је 1880. године основан пљеваљ- ски санџак — мутесарифлук тј. округ саседиштем у Пљевљима, који је обухватио казе Пљевља, Пријеноље и мундирлук - испоставу у Прибоју. Тосу места у којимасу се налазили аустро-угарски гарнизони. Исте године формиран је Новопазарски, одно- сно Сјенички санџак са седиштем у Сјеници, а који је обухватио казе: сјеничку, нововарошку, бјелопољску и доњоколашинску (територија данашњих општина Би- јело Поље и ..."
- ^ Dragoslav Srejović; Slavko Gavrilović; Sima M. Ćirković (1983). Istorija srpskog naroda: knj. Od Berlinskog kongresa do Ujedinjenja 1878-1918 (2 v.). Srpska književna zadruga. p. 263. https://books.google.com/books?id=L75BAAAAYAAJ. "Новопазарски санџак је већ 1879. издвојен из босанског вилајета са седиштем у Сарајеву и припојен косовском вилајету који је основан 30. јануара 1877. са седиштем у Приштини. Затим су турске власти 1880. образовале ..."
- ^ MacMillan, Margaret (2013). The War That Ended Peace. Random House. pp. 420–423.