የቶራ አስተኔ
የቶራ አስተኔ በሙሉ ጣት ሸሆኔ ክፍለመደብ ውስጥ የሆነ የጡት አጥቢ ሰፊ አስተኔ ነው።
በአስተኔው ውስጥ ያሉት ወገኖች እነዚህ ናቸው፦
- ሚዳቋ ቆርኬ (ኢምፓላ)- አንድ ዝርያ (አፍሪካ)
- ቆርኬ - አንድ ዝርያ (አፍሪካ)
- ሂሮላ ቆርኬ - አንድ ዝርያ (ኬንያ-ሱማሌ ጠረፍ ብቻ)
- ቶራ ፈረስ - ሁለት ዝርዮች (አፍሪካ)
- ቀይ ቆርኬ - ሦስት ዝርዮች (አፍሪካ)
- ዲባታግ - አንድ ዝርያ (ኢትዮጵያና ሶማሊያ ብቻ)
- ዘላይ ድኩላ (ስፕሪንግቦክ) - አንድ ዝርያ (ናሚቢያ ዙሪያ)
- የሕንድ ድኩላ - አንድ ዝርያ (ሕንድ ዙሪያ)
- ቀይ ድኩላ - አምስት ዝርዮች (አፍሪካ)
- የሚዳቋ ድኩላ ወገን - 8 ዝርዮች (አፍሪካ)
- ገረኑግ - አንድ ዝርያ (የአፍሪካ ቀንድ)
- የሜዳ ፍየል ወገን - የሜዳ ፍየል፣ ረጅም ቀንድ የሜዳ ፍየል፣ ዳማ ሜዳ ፍየል (አፍሪካ)
- የሞንጎሊያ ድኩላ ወገን - 3 ዝርዮች (ሞጎሊያ፣ ቲቤት፣ ቻይና)
- ሳይጋ ድኩላ - አንድ ዝርያ (እስያ)
- በይራ ድኩላ - አንድ ዝርያ (ጂቡቲ ዙሪያ)
- የንሹ - አራት ዝርዮች (ምሥራቅ አፍሪካ)
- ንጉሣዊ ድኩላ - አንድ ዝርያ (ምዕራብ አፍሪካ)
- ድንክ ድኩላ - ሁለት ዝርዮች (አፍሪካ)
- ሰስ - አንድ ዝርያ (አፍሪካ)
- ፌቆ - አንድ ዝርያ (አፍሪካ)
- የቡላ ድኩላ ወገን - ሦስት ዝርዮች (ደቡባዊ አፍሪካ)
- አራት ቀንድ ድኩላ - አንድ ዝርያ (ሕንድና ኔፓል)
- ሰማያዊ በሬ (ንልጋይ) - አንድ ዝርያ (ሕንድ)
- የእስያ ጎሽ ወገን - 5 ዝርዮች (እስያ)፤ የውሃ ጎሽ ለማዳ ነው።
- የበሬ ወገን - በሬ / ላም፣ ያክ፣ ዜቡ፣ ጋያል፣ የባሊ በሬ ለማዳ ሲሆኑ 4 አውሬ ዝዮችም አሉ።
- እንዝርት-ቀንድ ሳላ - አንድ ዝርያ (ቬትናም)
- ጎሽ - አንድ ዝርያ (አፍሪካ)
- የስሜን አሜሪካ ጎሽ ወገን - 2 ዝርዮች፣ አንዱ ከምሥራቅ አውሮፓ ነው።
- የአጋዘን ወገን - ድኩላ፣ የምኒልክ ድኩላ፣ ኣምበራይሌ፣ የደጋ አጋዘን፣ ኒያላ፣ 3 ሌሎች (አፍሪካ)
- የወንደቢ ወገን - ወንደቢና ታላቅ ወንደቢ (አፍሪካ)
- በሬ ዋሊያ (ታክን) - አንድ ዝርያ (ቡታን ዙሪያ)
- የዝባድ በሬ - አንድ ዝርያ (አርክቲክ ዙሪያ)
- የበርበር በግ - አንድ ዝርያ (ስሜን አፍሪካ)
- የአረቢያ ፍየል - አንድ ዝርያ (አረቢያ)
- የፍየል ወገን - ፍየል፣ ዋሊያ እና 6 ሌሎች
- የሂማላያ ፍየል - አንድ ዝርያ (ሂማላያ)
- የበግ ወገን - ለማዳ በግ እና 6 ሌሎች
- ንልጊሪ ፍየል - አንድ ዝርያ (ሕንድ)
- ሰማያዊ በግ - 2 ዝርዮች (ሂማላያ)
- ሰሮው (ፍየል-ድኩላ) - 6 ዝርዮች (እስያ)
- ጎራል (ፍየል-ድኩላ) - 4 ዝርዮች (እስያ)
- የተራራ ፍየል - አንድ ዝርያ (ስሜን አሜሪካ)
- ሻምዋ ዋልያ - 2 ዝርዮች (አውሮፓ)
- ተራ ሚዳቋ - 2 ዝርዮች (አፍሪካ)
- ሌሎች ሚዳቋዎች - ፪ ወገኖች (አፍሪካ)
- የፈረስ ፍየል ወገን - 2 ዝርዮች (አፍሪካ)
- ሳላ - 4 ዝርዮች (አፍሪካ)
- ነጭ ድኩላ - አንድ ዝርያ (ሳሃራ በረሃ)
- የቲቤት ድኩላ - አንድ ዝርያ (ቲቤት)
- አጋዘን ድኩላ - አንድ ዝርያ (ደቡብ አፍሪካ)
- የድፋርሳ ወገን - ድፋርሳና 5 ሌሎች (አፍሪካ)
- ብሆር - ሦስት ዝርዮች (አፍሪካ)
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |