የባዬ ስጋጃ
የባዬ ስጋጃ በባዬ፣ ፈረንሳይ የሚቀመጥ ስጋጃ ነው። ስጋጃው ከ1056 እስከ 1058 ዓም ድረስ፣ እስከ ሄስቲንግዝ ውግያ ድረስ የኖርማንዲ መስፍን («ዊሊያም አሸናፊ») ኢንግላንድን ለመውረር ያደረጋቸውን እርምጆች ያሳያል። ከዚሁም ዘመቻ ቀጥሎ ቀዳማዊ ዊሊያም ተብሎ የኢንግላንድ ንጉስ ሆነ፤ የኢንግላንድም ስራ ቋንቋ ለጊዜው ኖርማንኛ ፈረንሳይኛ ሆነ።
የስጋጃው ጽሑፍ ቋንቋ ሮማይስጥ ነው።
በጥር 2010 ዓም የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኤማንዌል ማክሮን ስጋጃውን ለመጀመርያው ጊዜ ለዩናይትድ ኪንግደም ለአራት አመት እንዲያበድረው አስታወቀ።