የቁራ ሻይ (Gaultheria procumbens፤ እንግሊዝኛ፦ Teaberry, Wintergreen, Checkerberry) በምሥራቅ ካናዳና በአሜሪካ አገራት በብዛት የሚበቅል የዱር ተክል ነው።

የቁራ ሻይ

ተክሉ ደግሞ በእንግሊዝኛ «የተራራ ሻይ»፣ «የምድር ሻይ» ወይም «የካናዳ ሻይ» ተብሏል። በጥንታዊ ኗሪዎች አልጎንኲያን ቋንቋዎች ለምሳሌ ሚግማቅኛ ተክሉ /ካቃጁ'ማናቅሲ/ «የቁራ ቅጠል» ተብሏል።

ተክሉ ለምድር ቅርብ ይጠብቃል፤ አንዳንዴም ትንንሽ ቀይ ፍሬዎችን ያፈራል። ፍሬዎቹ አይጎዱም፣ በተለይ በሽኮኮና ሌሎች እንስሳት ይበላሉ። ተክሉ ምንጊዜም በበረድ ወይም በሙቀት ወቅት ሁሌ-ለም አረንጓዴ ነው፣ 'Wintergreen' መባሉ ስለዚህ ነው።

ቅጠሎቹ እንደ ሻይ ቅጠል እንዲጠቀሙ፣ በፍልውሃ ተጨምረው ለሦስት ቀን ይቆዩ። ይህ ሻይ ከጥንት ጀምሮ እስከ ዛሬ በባሕላዊ መድኃኒት ይገኛል፣ ለደም ግፊትልብ ድካም፣ ወዘተ. ለማከም ወይም ለመከልከል ይጠጣል።

ይህ ዘዴ በቅጠሎቹ ያለውን ንጥረ ነገር ያስወጣል። ይህ ንጥረ ነገር Methyl salicylate ሲባል እንደ ሠው ሠራሽ አስፒሪን ተመሳሳይ ነው። እንዲሁም ንጥረ ነገሩ ለሳይንስ የታወቀው አስፒሪንም በላብራቶሪ የተፈጠረው በተለይ ከዚሁ ተክል ዕውቅና ወጣ።