የሸዋ ኣረም (Galinsoga parviflora) ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ተክል ነው።

የሸዋ አረም

የተክሉ ሳይንሳዊ ጸባይ ለማስተካከል

የሸዋ አረም እስከ 75 ሴንቲ ሜትር ድረስ ሊሆን ይችላል። ባለ ቅርንጫፍ እጽ፣ ፊት ለፊት የሆኑ ባለ አገዳ ቅጠሎቹ ዳርቻቸው ጥርስ ባለ ሚስማር ላይ ነው። አበቦቹ በትንንሽ ራሶች ናቸው፣ ራሱም በ3-8 ነጭ አበቢቶች ተከብቦ፣ እነዚህም አበቢቶች 1 mm ሆነው ሦስት ግርብ ያላቸው ናቸው። በመሃሉ ያሉት አበቢቶች ቢጫ ሲሆኑ ቱቦአዊ ቅርጽ አላቸው።[1][2]

በብዛት የሚገኝበት መልክዓ ምድር ለማስተካከል

ስሙ «የሸዋ» ቢባልም እንዲያውም መነሻው በፔሩ ነበረ። አሁን ወደ ብዙ አህጉራት ተስፋፍቶ በአጠቃላይ እንደ አረም ይቆጠራል። የሸዋ አረም በመላው ሸዋ፤ አርሲ እና ባሌ ይገኛል፡፡ ዱር በቀል ነው፡፡ መገኛው ኢትዮጵያ ነው፡፡

የተክሉ ጥቅም ለማስተካከል

ኮሎምቢያ አገር አበሳሰል «አሕያኮ» በሚባል ሾርባ አይነት ውስጥ እንደ ቅመም ይበላል። በሠላጣ ደግሞ ሊበላ ይችላል።

በኢትዮጵያ ባህላዊ መድሃኒት፣ የትኩስ ቅጠልና ህብራበባ ውጥ የቆዳ ቁስል ለማከም ይጠቀማል።[3]


  1. ^ Clapham, A.R., Tutin, T.G. and Warburg, E.F. 1968 Excursion Flora of the British Isles. Cambridge University Press. መለጠፊያ:ISBN
  2. ^ "Flora of China, Galinsoga parviflora Cavanilles, 1795.". Archived from the original on 2020-07-27. በ2017-07-10 የተወሰደ.
  3. ^ አማራ ጌታሁን - SOME COMMON MEDICINAL AND POISONOUS PLANTS USED IN ETHIOPIAN FOLK MEDICINE Archived ጁላይ 31, 2017 at the Wayback Machine March 1976 እ.ኤ.አ.