የማርያም ቅዳሴ ገፅ ፲

ዘቅዱስ ሕርያቆስ

የማርያም ቅዳሴ ገፅ ፲

ዘቅዱስ ሕርያቆስ


፶፱ ፤ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይሠራሉ ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያስማማሉ ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያከናውናሉ ።
፷ ፤ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይልካሉ ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያሰለጥናሉ ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ምስክር ይሆናሉ ።
፷፩ ፤ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሰውን ይስባሉ ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያለምዳሉ ።አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይመክራሉ ።
፷፪ ፤ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያነጻሉ ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያጸራሉ ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያከብራሉ ።
፷፫ ፤ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያጸናሉ ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያስጨክናሉ ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያስተምራሉ ።
፷፬ ፤ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይጋርዳሉ ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያለብሳሉ ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ባለምዋል ያደርጋሉ ።
፷፭ ፤ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይቀመጣሉ ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይፈርዳሉ ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይመረምራሉ ።
፷፮ ፤ እንዲህ እናምናለን እንዲህም እንታመናለን አንድነትን ሳንለይ የተለየ እንዳይሆን ። የተቀላቀለ እንዳይሆን እንለይ።
፷፯ ፤ እንደ አብርሃምና እንደ ይስሐቅ እንደ ያዕቆብም ሦስት የምንል አይደለም በገፅ ሦስት ሲሆን አንድ ነው እንጂ ።