የማርያም ቅዳሴ ገፅ ፲፩

ዘቅዱስ ሕርያቆስ

የማርያም ቅዳሴ ገፅ ፲፩

ዘቅዱስ ሕርያቆስ


፷፰ ፤ ከፍጥረት ሁሉ እንደሚቀድም እንደ አዳም አንድ የምንል አይደለም በባሕርዪው አንድ ሲሆን ሦስት ነው እንላለን እንጂ ።
፷፱ ፤ ክፉዎች አይሁድ ባለማወቃቸው የእግዚአብሔርን ገፅና አካል አንድ ነው የሚሉ በደለኞችን የይስማኤል ወገኖችንም እነሆ እንሰማቸዋለን ልቦናቸውን ያሳወሩ ናቸው ።
፸ ፤ አምላኮቻቸውም ብዙ አጋንንቶቻቸው ብዙ የሆኑ በጣዖት የሚያመልኩ አረማውያንን እንሆ እናያቸዋለን ።
፸፩ ፤ እኛ ግን በጎ ጐዳና የሚያስተምሩትን እንከተላለን ። ሐዋርያት እንዲህ እያሉ እንዳስተማሩን ።
፸፪ ፤ አብ ፀሐይ ነው ወልድ ፀሐይ ነው መንፈስ ቅዱስም ፀሐይ ነው ። ከሁሉ በላይ የሚሆን አንድ የእውነት ፀሐይ ነው ።
፸፫ ፤ አብ እሳት ነው ወልድ እሳት ነው መንፈስ ቅዱስም እሳት ነው ። በልዕልና ያለ አንድ የሕይወት እሳት ነው ።
፸፬ ፤ አብ ጎሕ ነው ወልድ ጎሕ ነው መንፈስ ቅዱስም ጎሕ ነው ። በብርሃኑ ፀዳል ጨለማ የራቀበት አንድ የጧት ጎሕ ነው ።
፸፭ ፤ አብ ጒንደ ወይን ነው ወልድ ጒንደ ወይን ነው መንፈስ ቅዱስም ጒንደ ወይን ነው ። ዓለሙ ሁሉ የጣፈጠበት አንድ የሕይወት ወይን ነው ።
፸፮ ፤ አብ ሐሊብ ነው ወልድ ሐሊብ ነው መንፈስ ቅዱስም ሐሊብ ነው ። ጭማሪ የሌለበት አንድ ሐሊብ እርሱ ነው ።