የማርያም ቅዳሴ ገፅ ፱

ዘቅዱስ ሕርያቆስ

የማርያም ቅዳሴ ገፅ ፱

ዘቅዱስ ሕርያቆስ


፶፫ ፤ የላከ አብን በህላዌ አባት እንደሆነ እናምናለን የተላከ ወልድንም በህላዌ ወልድ እንደሆነ እናምናለን ማኅየዊ መንፈስ ቅዱስንም በህላዌ መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ እናምናለን ሦስቱ ስም አንዱ እግዚአብሔር ነው
፶፬ ፤ አብርሃም ከይስሐቅ እንደሚበልጥ ይስሐቅም ከያዕቆብ እንደሚበልጥ አይደለም ለመለኮት እንዲህ አይደለም ። አብ ከልጁ አይበልጥምወልድም ከመንፈስ ቅዱስ አይበልጥም መንፈስ ቅዱስም ከወልድ አያንስም ወልድም ከአባቱ አያንስም ።
፶፭ ፤ አብርሃም በፍጥረት ሥርዓት ይስሐቅን እንደሚያዘው ይስሐቅም ያዕቆብን እንደሚያዘው አይደለም ። መለኮት እንዲህ አይደለም እባት በመሆን አብ ልጁን አያዝዘውም ወልድም ልጅ በመሆን አይበልጥም መንፈስ ቅዱስም ትክክል ነው ።
፶፮ ፤ መለኮት ግን አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስም ነው ። አንድ አምላክ አንዲት መንግሥት አንዲት ሥልጣን አንዲት አገዛዝ ነው ።
፶፯ ፤ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያስባሉ ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይናገራሉ ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይወዳሉ ።
፶፰ ፤ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይመክራሉ ።አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይናገራሉ ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይፈፅማሉ ።