የማርያም ቅዳሴ ገፅ ፬

ዘቅዱስ ሕርያቆስ

የማርያም ቅዳሴ ገፅ፬

ፀሎተ ሐሙስ.jpeg

Livre.png
ዘቅዱስ ሕርያቆስ

፲፰ ፤ ይልቁንም በዚች ቦታ ስለሞቱ አንቺ ስለነርሱ ተግተሽ አማልጂ ነፍሳቸውን ዕረፍት ሰጥቶ ያሳርፍ ዘንድ ።
፲፱ ፤ የድል ነሺዎች የሰማዕታት ቦታ በተባለ ሁሉ ዘንድ በብሩካን ጻድቃን ቦታና በትጉሀን መላእክት ቦታ በቦታው ሁሉ ዘንድ አንቺ ርስት ነሽ ስምሽም በእግዚአብሔር ዘንድ የሠለጠነ ነው ።
፳ ፤ የተቀመጣችሁ ተነሡ
፳፩ ፤ እግዚአብሔርን በመፍራት እንነሣ ምስጋናን የተመላች እርስዋን ከፍ ከፍ እናደርጋት ዘንድ እንዲህም እያልን እናመሰግናት ዘንድ ጸጋን የተሞላሽ ሆይ የደስታ መፍሰሻ ሆይ ዓይኖቻቸው ብዙዎች ከሆኑ ከኪሩቤል ክንፎቻቹው ስድስት ከሚሆኑ ከሱራፌል ይልቅ የሚበልጥ የመልክ ግርማ አለሽ ።
፳፪ ፤ ወደ ምሥራቅ ተመልከቱ ።
፳፫ ፤ እግዚአብሔር አብ በሰማይ ሆኖ ምሥራቅንና ምዕራብን ሰሜንና ደቡብን ዳርቻዎችንም ሁሉ በእውነት ተመለከተ ተነፈሰ አሻተተም እንድ አንቺ ያለ አላገኘም ። የአንቺን መዓዛ ወደደ ደም ግባትሽንም ወደደ ። የሚወደውን ልጁን ወደ አንቺ ሰደደ ።