የማርያም ቅዳሴ ገፅ ፫

ዘቅዱስ ሕርያቆስ

የማርያም ቅዳሴ ገፅ ፫

ፀሎተ ሐሙስ.jpeg

Livre.png
ዘቅዱስ ሕርያቆስ

፲፫ ፤ በቀናች ሃይማኖት ስላረፉ ስለ ቅዱሳን ሰማዕታት ሁሉ ጳውሎስ ጢሞቴዎስ ሲላስና በርናባስ ቲቶና ፊሊሞንና ቀለምንጦስም ሰባ ሁለቱ አርድዕት አምስት መቶ ባልንጀራዎች ሃይማኖታቸው ስለ ቀና ስለ ሦስት መቶ አሥራ ስምንቱ ።
፲፬ ፤ እሊህንም ሁሉንም ለአንተ ወገን ሊሆኑ አስባቸው ፣ ብፁዕ ወቅዱስ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት አባ.... ብፁዕ ሊቀ ጳጳስ አባ.... አስባቸው በሕይወታቸውም ትጠብቃቸው ዘንድ ኃጢያታቸውንም ይቅር ትላቸው ዘንድ እኛንም በእነርሱ ጸሎት ትምረን ዘንድ ለዘላለሙ ።
፲፭ ፤ ጸሎተ ቡራኬ ፣ ቅዳሴ ሐዋርያት ቁ ፲ - ፳፩ ።
፲፮ ፤ የጳጳሳቱን አለቆች ጳጳሳቱንና ኤጲስ ቆጶሳቱን ቀሳውስቱንና ዲያቆናቱን የክርስቲያንንም ወገኖች ሁሉ አቤቱ ማራቸው ይቅርም በላቸው ።
፲፯ ፤ አማላጅቱ ሆይ እሊህንም ሁሉንም ከልጅሽ ዘንድ አማልጂ የጳጳሳትንና የሊቃነ ጳጳሳትን የኤጲስ ቆጶሳትን ሁሉ ነፍስ ያሳርፍ ዘንድ የቀሳውስትንና የዲያቆናትንም ዕውነተኛውን የቃል ጎዳና የሚያቀኑ ። ነገሥታትና መኳንንቱን መሳፍንቱንም በሥልጣን የሚኖሩትን ወራዙትንና ደናግልን መነኮሳትንምባለጠጋውንና ድሀውን ታላቁንና ታናሹን ባልቴቱንና አባት እናት የሞቱበትን መጻተኛውንና ችግረኛውን አስቀድሞ ከቤተክርስቲያን ማኅበር ተለይተው ያረፉትን የክርስቲያንንም ወገኖች ሁሉ ።