የመዋቅር ትንታኔ
የመዋቅር ትንታኔ (structural analysis) የአካላዊ ህጎች ስብስብ ሲሆን በሒሳብ ህጎች ጋር በማጣመር ለመዋቅሮች አሰራር መፍትሄ የሚሰጥ የስሌት አይነት ነው። የዚህ የመዋቅር ስሌት ዋናው ግቡ የሚሰሩት መዋቅሮች ለሚገለገሉበት ድልድይ፣ ሕንፃ፣ አየር ማረፊያ አልያም መኪና በቂ ጥንካሬ እንዳለው ማረጋገጥ ነው። ስሌቱ በዋናነት በሜካኒክስ (mechanics) እና ዳይናሚክስ (dynamics) የትምህርት ዘርፎች ላይ በብዛት ጥቅም ላይ የሚውል ነው። ዋናው ቃላዊ የስሌቱ አካል በመዋቅሩ ላይ በተለያዩ መጠኖች እና አይነቶች በሚተገበሩ ጫናዎች ለሚፈጠሩት እንደ ጉልበት (forces)፣ ቅርጸተ ለውጥ (deformations) ወይም ጭንቅ (stresses) ስሌት ዋጋ መስጠት ነው።
የአወቃቀር ምህንድስና የህንጻዎችን፣ የድልድዮችን፣ የማማዎችን፣ የመንገድ ማቋረጫ ድልድዮችን፣ የዋሻዎችን፣ በባህርና ላይ የሚገነቡ ለነዳጅ ወይም ለዘይት ማውጫ የሚያገለግሉ ሰው ሰራሽ መሬቶችን እና ማማዎችንና እንዲሁም እነኚህን የመሳሰሉ የግንባታ አካላትን በተመለከተ የአወቃቀር ንድፍና (structural design) የአወቃቀር ትንታኔ (structural analysis) ላይ የሚያተኩር የሲቪል ምህንድስና ዘርፍ ነው።
የአወቃቀር ትንታኔ (structural analysis) ጉልበቶች በግንባታ አካላት ላይ የሚያሳድሩትን ተጽእኖ መመዘን ላይ ትኩረት ያደርጋል። የአወቃቀር ምህንድስና በግንባታ አካላት ላይ የሚያርፉ ጉልበቶችን ለምሳሌ የራሱ የግንባታ አካሉ ክብደት፣ በግንባታ አካሉ ላይ የሚያርፉ ሌሎች ቋሚና ተቀሳቃሽ ክብደቶች፣ የንፋስ ግፊት ፣ የሙቀት ለውጥ፣ የውሃ ግፊት፣ የመሬት ጫና፣ የመሬት ርእደት፣ በረዶ እና የመሳሰሉትን የመለየትና፣ በእነኝህ ጉልበቶች አማካኝነት በግንባታ አካላቱ ውስጥ የሚከሰቱ ውስጣዊ ጫናዎችንና ጉልበቶችን (internal stresses and forces) የማስላትና የግንባታ አካላቱ እነኝህን ጉልበቶች ተቋቁመው አገልግሎት እንዲሰጡ መጠናቸውንና የሚሰሩበትን ቁስ መንደፍ ላይ ያተኩራል። የአወቃቀር ምህንድስና ባለሙያው የግንባታ አካላቱ ተጠቃሚዎችን ደህንነትን በሚጠብቅ መልኩ (llimit state of carrying capacity) እንዲሁም ግንባታ አካላቱ ከተሰሩበት አላማ አንጻር የሚጠበቅባቸውን አገልግሎት እንዲሰጡ አድርጎ (limit state of serviceablity) መንደፍ ይጠበቅበታል።
እንደ ንፋስ እና የመሬት ርእደት አይነት ጉልበቶች በቀላሉ ለመተንበይ አስቸጋሪ በመሆናቸው በአወቃቀር ምህንድስና ስር እንደ ንፋስ ምህንድስና እና የመሬት ርእደት ምህንድስናን የመሳሰሉ ንኡስ ዘርፎች እንዲፈጠሩ ምክንያት ሆኖዋል።
በአወቃቀር ምህንድስና ውስጥ የንድፍና የትንታኔ ስራ የግንባታ አካሉ ቋሚ ጉልበቶችን ፣ተለዋዋጭ ጉልበቶችን (እንደ ንፋስና የመሬት ርእደት ያሉ) ወይም ጊዜያዊ ጉልበቶችን (ለምሳሌ በግንባታ ጊዜ ጥቅም ላይ የሚውሉ የግንባታ ማሽኖች ክብደት፣ በግንባታ አካሉ ላይ በተንቀሳቃሽ ነገሮች አማካኝነት ሊከሰቱ የሚችሉ ግጭቶች እና የመሳሰሉት) ለመሸከም የሚያስፈልገውን ጥንካሬና ጠጣርነት መወሰን እንዲሁም የግንባታ አካሉ ሚዛኑን ጠብቆ መቆም መቻሉን ማረጋገጥ ያካትታል። ከዚህም በተጨማሪ የንድፍና ትንታኔ ስራ የግንባታውን ዋጋ መተመን፣ የግንባታውን ተግባራዊነት ማረጋገጥ፣ ግንባታው ውበት የተላበሰ መሆኑን ማረጋገጥ እንዲሁም የሃብት አጠቃቀምና የተፈጥሮ ሚዛንን በጠበቀ መልኩ ግንባታው እንዲከናውን ማስቻልን ያካትታል።
መዋቅሮች እና ጫናዎች
ለማስተካከልየመዋቅሮች ምደባ
ለማስተካከልአስርዮሽ
የስሌት መንገድ
ለማስተካከልገደቦች
ለማስተካከልመደበኛው መንገድ
ለማስተካከልየማጠጋጋት መንገድ
ለማስተካከልይዩ
ለማስተካከልጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |
ማጣቀሻዎች
ለማስተካከል- Impact - Dynamic Finite Element Program Suite, for dynamic events like crashes, written in Java, GNU license
- A Historical Outline of Matrix Structural Analysis: A Play in Three Acts Archived ጁን 29, 2007 at the Wayback Machine
- Probabilistic assessment of structures using Monte Carlo simulation by Jan Hlavacek
- FEM Applications in Structural Analysis. AVI-gallery at CompMechLab site, St.Petersburg State Polytechnical University, Russia Archived ጃንዩዌሪ 27, 2009 at the Wayback Machine
- Frame3DD open source 3D structural analysis program
- Ocframe open source 2D structural analysis in GNU Octave