ዥን-ፖል ሳትራ
ዦን-ፖል ሳትራ (ሰኔ 21, 1905 – መጋቢት 15, 1980) ፈረንሳዊ ኅልውነት (ኤግዚስቴንሺያሊዝም) ፍልስፍና አራማጅ የነበረ ሰው ነው። ከፍልስፍናው ጎን ለጎን ፊልሞች፣ ልብ ወለዶች፣ የስነ ጽሁፍ ግምገማና ተውኔቶችን ይደርስ ነበር።
የህይወት ታሪክ
ለማስተካከልሳትራ ፓሪስ ፈረንሳይ ሲወለድ፣ እዚያው ተምሮ 1928ዓ.ም. ላይ ከዩኒቨርሲቲ በፍልስፍና ዶክትሬት ተመርቋል። ቀጥሎም ለ2 አመት የፈረንሳይን ጦር ተደባልቆ በውትድርና አገልግሏል።
በ1938 በደረሰው ልቦለድ፣ ሳትራ የኅልውነትን ፍልስፍና ነጥቦች በሚያሳይ መልኩ ስለ ሰው ልጅ ነጻነት ዘግቧል።
በ1939 ሳትራ የፈረንሳይን ሰራዊት ተቀላቅሎ የጀርመንን ናዚ ሰራዊት ሲዋጋ በ1940 ዓ.፣ም. ተማረከ። ለሚቀጥሉት 9 ወራት በእስር አሳለፈ። ከእስር ከተለቀቀ በኋላ በአስተማሪነት ስራው ቀጠለ። በ1943 ኅልውነትና ምንምነት የተሰኘውን መጽሐፉን አሳተመ። በመጽሐፉ የሰው ልጆች ለሚኖሩበት አገር ወይንም ማህበረሰብ ደንቦች በጣም ተገዥ ከሆኑ፣ የራሳቸውን ውሳኔ ማሳለፍ ያቅታቸዋል የሚል ነጥብን ለአንባቢወቹ ለማሳየት ይሞክራል።
በ1945 ዘመናዊ ጊዜ የተሰኘውን ጋዜጣ በማቋቋም ስለ ፖለቲካ፣ ኪነት እና ሥነ ፅሑፍ ብዙ ጽሑፎችን ያቀርብ ነበር።
በ1946 ኅልውነት ሰውነት ነው የተሰኘውን መጽሐፉን በማሳተም የኅልውነትን ፍልስፍና ለማብራራት ሞክሯል። ኅልውነት ስለ ሰው ልጅ ነጻነት የሚተጋ የፍልስፍና አይነት ነው።
በ50 ና 60ወቹ ሳትራ በፈረንሳይ ፖለቲካ እጅግ ተሳታፊ ሆነ። ፈረንሳይ የቀድሞ ቅኝ ግዛቷን አልጀሪያን ለቃ እንድትወጣ ይወተውት ነበር። የቪየትናምን ጦርነት አውግዟል።
ሳትራ በ1980 ሲያርፍ ለቀብሩ 50፣000 ሰው ተገኝቶ ነበር። የተቀበረውም ፓሪስ፣ ፈረንሳይ ነበር።